የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የአገራችንን የግብርና ክፍለ ኢኮኖሚ ለማሳደግ
የሚያስችሉ የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ለግብርና ልማት ተጠቃሚዎች በማድረስ ረገድ
ከፍተኛ ሀገራዊ ተልዕኮ የተሰጠው ተቋም ሲሆን ኢንስቲትዩት ሲሆን ይህንኑ ተልዕኮ ለመወጣት
ተቋማዊ አደረጃጀቱን በየጊዜው እየፈተሸ ማሻሻል እንዲሁም አደረጃጀቱን በብቃት የሚያስፈጽም
የምርምር አመራር መመደብ አስፈላጊ መሆኑ ይታመናል፡፡
በዚሁ መሰረት በመሆኑም ከዚህ በፊት በኢንስቲትዩቱ ፀድቆ በሥራ ላይ የዋለው የምርምር
አመራር ምደባ መመሪያ በትግበራ ሂደት በርካታ ክፍተቶች ያሉት መሆኑን በመፈተሽ እነዚህን
ክፍተቶች በሚያርም መልኩ መመሪያውን ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
ስለሆነም በሥራ ላይ ባለው መመሪያ ላይ ያጋጠሙ ክፍተቶችን ማለትም አንዳንድ የመመዘኛ
መስፈርቶች ግልጽ ያለመሆን እና ለአሰራር አመች ሆነው አለመገኘታቸው፤ በመመሪያው ውስጥ
የምርምር አመራርን የማይመለከቱ የምደባ መስፈርቶችን ማስተካካል በማስፈለጉ፤ መመሪያው
የምርምር ዳይሬክተሮችን አመዳደብ ብቻ የያዘ በመሆኑ ሌሎች የምርምር አመራሮችን ለመመደብ
የሚያስችል አለመሆኑ እንዲሁም ከጊዜው ጋር የሚሄዱ አዳዲስ አሰራሮችን በመመሪያው ውስጥ
ማካተት በማስፈለጉ በኢንስቲትዩቱ ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 527/2015 አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ
21 በተሰጠው ተቋማዊ የአሰራር ስርዓቶችን የመዘርጋት ሥልጣንና ተግባር መሰረት ይህ
የምርምር አመራር ምደባ መመሪያ ተሻሽሎ ወጥቷል፡፡