Vacancy Announcement
The Ethiopian Institute of Agricultural Research (EIAR) would like to invite qualified and competent applicants for the following positions. Positions: One (1), Two (2), Three (3) and Four (4) Terms…
The Ethiopian Institute of Agricultural Research (EIAR) would like to invite qualified and competent applicants for the following positions. Positions: One (1), Two (2), Three (3) and Four (4) Terms…
“ICT from Supporting to Core Activity” The Ethiopian Institute of Agricultural Research (EIAR) conducted a workshop in Adama focused on the Digital Agriculture Research. The workshop was attended by senior…
የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩትጥቅምት 3ዐ ቀን 2ዐ17 ዓ.ም. /ሆለታ/ በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የሆለታ ምርምር ማዕከል ጥቅምት 3ዐ ቀን 2ዐ17 ዓ.ም. የአርሶ አደሮች የመስክ ቀን ፕሮግራም አካሄደ፡፡ ፕሮግራሙን በእንኳን ደህና…
የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩትየማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት/ጉራጌ ዞን በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የወልቂጤ ምርምር ማዕከል ህዳር 3 ቀን 2ዐ17 ዓ.ም. በምርምር እና በአርሶ አደር ማሣ የተሠሩ የዘር ብዜት ሥራ፣ የኩታ…
**********************************************************November 4.2024; Addis AbabaThe third training cycle, titled "Harnessing Artificial Intelligence Applications for Agricultural Research in Ethiopia: AI for Resilient Food Systems," began at EIAR's Hiruy Hall, with the participation…
***********************************************የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩትጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የ2017 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የጠቅላላ ማኔጅመንት መደበኛ ስብሰባ ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም በተቋሙ ሕሩይ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡ስብሰባውን በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር የከፈቱት በተቋሙ የም/ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ድሪባ ገለቲ ሲሆኑ ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ንጉሤ ደቻሳ በፓዎር ፖይንት የታገዘ የመክፈቻ ንግግር አቅርበዋል፡፡ በመቀጠልም በዋናው መ/ቤት የሴክተር ዳይሬክተሮች በተቀመጠላቸው መርሀ-ግብር መሠረት የበጀት ዓመቱን የ1ኛ ሩብ ዓመት የአፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ ሪፖርቱ የምርምር ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ (የምርምር ስራና ውጤቶችን) በተመለከተ፤ የቴክኖሎጂ ጥበቃና ሽግግር ዕቅድ አፈጻጸምን (መነሻ ቴክኖሎጂ፣ ሰርቶ ማሳያ፣ ስልጠና፣ ቴክኖሎጂ ብዜት፣ ቴክኖሎጂ ማስፋትን) በተመለከተ፤ የዘርፈ-ብዙ (cross-cutting) ስራዎች አፈጻጸምን በተመለከተ፤ የአስተዳደርና የማኔጅመንት ዕቅድ አፈጻጸምን በተመለከተ፤ (የፋይናንስ አፈፃፀም፣ የሰው ሀብት አስተዳደር፣ የመሰረተ ልማት ሂደቶችን እና የውጭ ትብብር)፤ እንዲሁም የዋና ዋና የአፈጻጸም ማነቆዎች/ተግዳሮቶች በሪፖርት ለግምገማ ቀርበዋል፡፡ በሪፖርቱ መሠረት ውይይት ከተካሄደ በኋላ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮችና በሥራ ላይ ባጋጠሙ ችግሮች ላይ የመፍትሄ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
October 31, 2024EIAR, Addis AbabaAvocado feasibility and suitability study, consultation, and validation session were held at EIAR's HiruyHall. In his welcoming remarks, Mr. Abdella Negash, Lead Executive for Horticulture Development…
****************************************የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩትጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም.በኢንስቲትዩቱ ለአራት ዓመታት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ክቡር ዶ/ር ፈቶ ኢስሞ የሽኝት ፕሮግራም ተደረገላቸው፡፡ የሽኝት ፕሮግራሙ ዶ/ር አበራ ደሬሳ የተቋሙ የቦርድ ሰብሳቢ፤ ዶ/ር ብርሃኔ ገ/ኪዳን የተቋሙ የቦርድ አባል፤ የማዕከላት አመራሮች፤ ሠራተኞችና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት ተከናውኗል፡፡ በአንፃሩም አዲስ ለተሾሙት ፐሮፌሰር ንጉሴ ደቻሳ የአቀባበል መርሐ-ግብር ተከናውኗል፡፡ በሽኝት እና በአቀባበል መርሐ-ግብሩ ላይ የኢንስቲትዩቱ የም/ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ድሪባ ገለቲ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ሽኝት ለሚደረግላቸው ለክቡር ዶ/ር ፈቶ ኢስሞ የመልካም ዕድል ምኞት አዲስ ለተሾሙት ፐሮፌሰር ንጉሴ ደቻሳ ደግሞ መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው በራሣቸውና በተቋሙ ሠራተኞች ስም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡በመርሐ-ግብሩ የተቋሙ የዋና መስሪያ ቤትና የማዕከላት ሰራተኞችና አመራሮች ለክቡር ዶ/ር ፈቶ ኢስሞ የስጦታ ማስታወሻ አበርክተውላቸዋል፡፡
ጥቅምት 16 ቀን 2017 ዓ.ም. የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት/አሰላ በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የቁሉምሳ ግብርና ምርምር ማዕከል በለሙ እና ቢልቢሎ ወረዳ በቆጂ ከተማ እንዲሁም በምርምር ማዕከሉ የተለያዩ የባለድርሻ አካላት በተገኙበት ማለትም የኦሮሚያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን፤ የአሰላ ብቅል ፋብሪካ ኃላፊዎች፣ የአሰላ ከተማ አስተዳደር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊዎች፤ የማዕከሉ ተመራማሪዎች እንዲሁም የዋናው መ/ቤት አመራሮች በተገኙበት የመስክ ጉብኝት አካሂዷል፡፡ ጉብኝቱ በአካባቢው ባህል መሠረት በአገር ሽማግሌዎች ምርቃት ተጀምሯል፡፡ የመስክ ጉብኝት ቀንኑ አስመልክቶ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የቁሉምሳ ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ደበሌ ደበላ ሲሆኑ የመስክ ጉብኝቱን ለመታደም የተገኙትን እንግዶች አመስግነዋል፡፡ ቀጥለውም የቁሉምሳ ግብርና ምርምር ማዕከል ከተቋቋመበት እ.ኤ.አ ከ1960ዎቹ ጀምሮ በተለይ በዳቦ ስንዴ፤ በብቅል እና በምግብ ገብስ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ከፍተኛ ውጤቶችን ሲያስመዘግብ ቆይቶ በአሁኑ ወቅት በአገር ደረጅ የስንዴ የልህቀት ማዕከል እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ በመቀጠልም በመጀመሪያ የመስክ ጉብኝት በተካሄደበት የቦቆጂ ንዑስ ጣቢያ የስንዴ እና የገብስ የመነሻ ዘር ማባዣ ማሣን እንዲሁም የአፈሩን ለምነት ለመጠበቅ ያስችል ዘንድ በፈረቃ የሚለሙ የባቄላ፣ የአተር እና የተልባ ማሣዎች ለጉብኝት መቅረባቸውንና የምርታማነት መጠንን በዝርዝር አሰረድተዋል፡፡ በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የም/ም ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ድሪባ ገለቲ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ኢንስቲትዩቱ በአገራችን ከሚገኙ ትላልቅ ተቋማት አንዱ ሲሆን ቴክኖሎጂ በመልቀቅ፤ የመነሻ ዘር በማባዛትና በማሰራጨት፤ ቴክኖሎጂ በማስተዋወቅ እና የአቅም ግንባታ በመገንባት ረገድ የተሰጠውን ተለልዕኮ በተግባር ከሚወጡት ዋነኛው ነው ብለዋል፡፡ የቁሉምሳ የግብርና ምርምር ማዕከልም በኢንስቲቲዩቱ ስር ከሚገኙ ትልልቅ ማዕከላት ትልቁ እንደዚሁም ከፍተኛ ስራዎችን ከሚሰሩት መካከል አንዱ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡ በማዕከሉ ግቢ እና በሌሎች ንዑስ ጣቢዎች ጉብኝት ከተካሄደ በኋላ ከተለያዩ የባለድርሻ አካላት አበረታችና ገምቢ ግብረ-መልስ ቀርቧል፤ በመጨረሻም ውይይት የተደረገ ሲሆን በኢንስቲትዩቱ የም/ም/ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ድሪባ ገለቲ ሰፋ ያለ ማብራሪያና የስራ መመሪያ ተሰጥቶ የዕለቱ መርሐ-ግብር ተጠናቋል፡፡
EIAR/July 31/2024, Addis Abeba The Ethiopian Institute of Agricultural Research (EIAR) organized a technical workshop focused on Wheat Fusarium Head Blight (FHB) Disease, held at the Nexus Hotel from July…