በተቋሙ የበጀት ዓመቱ የ1ኛ ሩብ ዓመትጠቅላላ የማኔጅመንት መደበኛ ስብሰባ ተካሄደ
***********************************************የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩትጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የ2017 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የጠቅላላ ማኔጅመንት መደበኛ ስብሰባ ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም በተቋሙ ሕሩይ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡ስብሰባውን በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር የከፈቱት በተቋሙ የም/ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ድሪባ ገለቲ ሲሆኑ ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ንጉሤ ደቻሳ በፓዎር ፖይንት የታገዘ የመክፈቻ ንግግር አቅርበዋል፡፡ በመቀጠልም በዋናው መ/ቤት የሴክተር ዳይሬክተሮች በተቀመጠላቸው መርሀ-ግብር መሠረት የበጀት ዓመቱን የ1ኛ ሩብ ዓመት የአፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ ሪፖርቱ የምርምር ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ (የምርምር ስራና ውጤቶችን) በተመለከተ፤ የቴክኖሎጂ ጥበቃና ሽግግር ዕቅድ አፈጻጸምን (መነሻ ቴክኖሎጂ፣ ሰርቶ ማሳያ፣ ስልጠና፣ ቴክኖሎጂ ብዜት፣ ቴክኖሎጂ ማስፋትን) በተመለከተ፤ የዘርፈ-ብዙ (cross-cutting) ስራዎች አፈጻጸምን በተመለከተ፤ የአስተዳደርና የማኔጅመንት ዕቅድ አፈጻጸምን በተመለከተ፤ (የፋይናንስ አፈፃፀም፣ የሰው ሀብት አስተዳደር፣ የመሰረተ ልማት ሂደቶችን እና የውጭ ትብብር)፤ እንዲሁም የዋና ዋና የአፈጻጸም ማነቆዎች/ተግዳሮቶች በሪፖርት ለግምገማ ቀርበዋል፡፡ በሪፖርቱ መሠረት ውይይት ከተካሄደ በኋላ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮችና በሥራ ላይ ባጋጠሙ ችግሮች ላይ የመፍትሄ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡