COVID-19 Response
 

የኮቪድ-19 ኮሮና ቫይረስ ወረርሽ መከላከል ስራ ሪፖርት

በዓለም ብሎም በአገራችን የኮቪድ- 19 ወረርሽኝ በመከሰቱ ምክንያት የበሽታዉን ስርጭት ለመግታትና ለመከላከል እንደ ሀገር የታቀዱ ስራዎችን ለመተግበር የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የስጋት ቅነሳ ስልት እና የድርጊት መርሃ ግብር አዘጋጅቶ ወደ ሁሉም ማዕከላት በማውረድ  የቅድመ መከላከል እና የወረርሽኝ ቁጥጥር ስራ በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡  በአገሪቱ የኢኮኖሚውም ሆነ የምግብ ዋስትና በሆነው ግብርና ላይ የበሽታው ስርጭት እንዳይስፋፋና የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ በአርሶ/አርብቶ አደሩ ዘንድ ግንዛቤ በመፍጠርና የመከላከል ስራውን ለማጠናከር እንዲሁም የተቋሙ የምርምር ባሙያዎች ራሣቸውን ጠብቀው ለአርሶ/አርብቶ አደሩ እንዲሁም ለተለያዩ ማህበረሰብ  ወረርሽኙን በመከላከል እና በቁጥጥር የዓመቱ የእርሻ ስራ እንዴት መሠራት እንዳለበት የተወሰዱ እርምጃዎችና ያጋጠሙ ችግሮች በጥቅል እና በዝርዝር ሪፖርት እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡ 

 

በሁሉም ማዕከላት የተከናወኑ ተግባራት

·        አምስት አባላት ያሉት ግብረ-ኃይል መቋቋም፤

·        የሠራተኛ ቁጥር መቀነስ፤

·        የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች ዝግጅት፤ (ፌስ ማስክ፣ ሣሙና…)

·        የሰርቪስ ተሣፋሪ ቁጥር መወሰን፤

·        የሣኒታይዘር በማዕከሉ መዘጋጀት፡፡

 

በሁሉም ማዕከላት ያጋጠሙ ችግሮች

·        ስራ እንዳይገቡ የተደረጉ ሰራተኞች ወደ ሥራ ለመግባት ማስቸገር እና የመገለል ስሜት መፈጠር፤

·        ለግዥ ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት ስጋት እና ፍርሃት መፈጠር፤

·        ለቫይረሱ መከላከያ፣ የጥንቃቄ እና የንፅህና መጠበቂያ ግብዓት እጥረት፡፡