በኢንስቲትዩቱ በሕዝብ ግንኙነትና አእምሮአዊ ንብረት ባለቤትነት ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ የግራፊክስና ዲዛይን ሥልጠና ለሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎችና ከተለያዩ ማዕከላት ለተውጣጡ የኮምዩኒኬሽን እንዲሁም የቴክኖሎጂ ስርፀትና ኮሜርሻላይዜሽን ተመራማሪዎች ከሰኔ 12-16 ቀን 2009 ዓ/ም በኢንስቲትዩቱ ዋና መ/ቤት ተሰጠ፡፡

 

ሥልጠናው በPhotoshop እና InDesign ሶፍትዌሮች ላይ አጠቃቀም ያተኮረ ሲሆን ሠልጣኞች በሶፍትዌሮቹ አጠቃቀም ዙሪያ ያለባቸውን ክፍተት በመሙላትና ክህሎታቸውን በማዳበር የምርምር ውጤቶችን በተለያዩ የሕትመት ውጤቶች ለሕብረተሰቡ ለማስተዋወቅ የሚረዳቸው መሆኑን የገለጹት የሕዝብ ግንኙነትና አእምሮአዊ ንብረት ባለቤትነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፍስሐ ዘገዬ ናቸው፡፡ ለማህበረሰቡም ሆነ የምርምሩን ውጤት ተጠቃሚ ለሆኑ አርሶ አደሮች የሚዘጋጁ ፅሑፎች፣ ፖስተሮች፣ ባነሮች እና የመሳሰሉት በግራፊክስ ሶፍትዌር የታገዙ ቢሆኑ የተጠቃሚዎችን ፍላጎት የመጨመር ሚና የሚኖራቸው ከመሆኑ አኳያ ስልጠናው አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

 

ሠልጣኞቹ በሰጡት አስተያየት እንዲዚህ ዓይነቱ ሥልጠና ለተሰማሩበት ሙያ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረውና ክህሎታቸውን ያሳደገ በመሆኑ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡