ለኢንስቲትዩቱ አሽከርካሪዎችና የሥራ ኃላፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ

በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ውስጥ ለሚገኙ አሽከርካሪዎች፣ መካኒኮች፣ ከሥራውጋር ተያያዥነት ያለው ሥራ ለሚሰሩ ባለሙያዎችና ለኢንስቲትዩቱ የሥራ ኃላፊዎች ስለ መንገድ ደህንነትና በተሽከርካሪ አያያዝና አጠባበቅ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከሰኔ 21- 22 ቀን 2009 ዓ/ም በኢንስቲትዩቱ ዋና መ/ቤት ተሰጥቷል፡፡

የስልጠናው ዓላማ በአሁኑ ጊዜ በአገሪቷ እየታየ ባለው የመንገድ ትራፊክ አደጋ መጨመር የተነሳ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰ በመሆኑ በዚሁ ዙሪያ ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው፡፡ ከዚሁ በመነሳት  ስለ አዲሱ የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ፣ ስለ ተሽከርካሪ አያያዝና ስለ ትራፊክ አደጋዎች መንስኤ የግንዛቤ ማስጨበጫዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ 

የትራፊክ አደጋ የተለያዩ ምክንያቶች ቢኖሩትም ከዚህ መካከል ከግንዛቤና ከዕውቀት ማነስ ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ አደጋዎችን ለመቅረፍ አሽከርካሪዎችና ሕብረተሰቡ ላይ በሰፊው መሰራት እንዳለበት የገለፁት ለግንዛቤ ማስጨበጫው ስልጠና እንዲሰጡ የተጋበዙት ኢንስፔክተር አሰፋ መዝገቡ ናቸው፡፡ ኢንስፔክተሩ እንዳሉት አሽከርካሪዎች የቀን ተቀን ትልቅ ኃላፊነት ያለባቸው በመሆኑና ክቡሩን የሰው ሕይወት ይዘው የሚንቀሳቀሱ በመሆኑ ሰፊ ትዕግስት እንዲኖራቸው ለሰልጣኞቹ አሳስበዋል፡፡

 

ሰልጣኞቹ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በተሰጠው ስልጠና ሰፊ ግንዛቤ ማግኘታቸውንና ክህሎታቸውንና ዕውቀታቸውን ያሳደገላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡