የአየር ንብረት ለውጥን  መቋቋም በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ባለድርሻ አካላት በጋራ ተወያዩ

የኢትዮጵያግብርናምርምርኢንስቲትዩት ፤ከእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር ፤ከብሄራዊ የሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ እና ከኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲጋርበመተባበርየአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይያተኮረውይይት ከሰኔ 25-27/2009 ዓ.ም በኢሊሌ ሆቴል አካሄደ፡፡ 

ከተለያዩ የግብርና ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎችን ያሳተፈው ይህ የምክክር መድረክ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቋቋም አርሶ አደሮች መረጃወችን እንዴት ማግኘት እንዳለባቸው እና መረጃውም ለአርሶ አደሩ ለአርብቶ አደሩ እና ለከፊል አርብቶ አደሩ በሚገባው ቋንቋ እንዴት ተደራሽ መሆን እንዳለበት መክረዋል፡፡

የአየር ንብረት ለውጥ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እንዲከሰት ምክንያት መሆኑን ተሳታፊወቹ በማንሳት በተለይም ዋነኛ ኢኮኖሚያቸው ግብርና ለሆነውና በማደግ ላይ ላሉት የአፍሪካ ሀገራት ድርቅና ርሀብ እንዲከሰት እና እንዲባባስ የአየር ንብረት ለውጡ እንደ ዋና ምክንያጥ ተጠቅሷል፡፡የግብርናውን ዘርፍ እያጠቃ ያለው የአየር ንብረት መለዋወጥ ነው ያሉት ተሳታፊወቹ ለዚህ ደግሞ በግብርናው ዘርፍ የተሰማሩ አርሶ አደሮች፤ አርብቶ አደሮች  እና ከፊል አርብቶ አደሮች ስለ አየር ጸባይ ለውጥ በቂ የሆነ የሜቲወሮሎጂ መረጃ እንዲያገኙ ድጋፍ መደረግ አለበትም ብለዋል፡፡

ሌላው ደግሞ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ለመቋቋም በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የተወያዩ ሲሆን ችግሩን ለመቅረፍም አርሶ አደሮች አግሮ ሜትሮሎጂ መረጃዎችን በቀላሉ እንዲያገኙ ማድርግ እንደመፍትሄ ከተቀመጡ ሀሳቦች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ይህንን የአየር ጸባይ መለዋወጥ ሂደት ለአርሶ አደሩ፤ ለአርብቶ አደሩ እና ለከፊል አርብቶ አደሩ  በሚገባው መንገድና በቀላል ቋንቋ ማስረዳት ደግሞ ሌላው ነው፡፡የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም በዘርፉ እውቀት ያላቸው ምሁራንን በማፍራት አርሶ አደሩ፤አርብቶ አደሩ እና ለከፊል አርብቶ አደሩ  የተሻለ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚና እውቀት ያለው እንዲሆን የበኩላቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡

 

በዚህየውይይት መድረክ ላይየባለድረሻ አካላት  የበላይአመራሮች፣የምርምርዳይሬክተሮች፣ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጡ የተለያዩ ምሁራን እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው አካላትተሳታፊነበሩ፡፡