COVID-19 Response
 

የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

 በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ለዋናው መ/ቤት እና ለማዕከላት የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ተከታታይ የቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች ከጥቅምት 17-18 ቀን 2014 ዓ.ም. የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ዶ/ር ድሪባ ገለቲ የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የምርምር ም/ዋና ዳይሬክተር በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው እንዳሉት የህዝብንና የመንግስትን ሀብት ለግል ጥቅም ማዋል ወንጀል እንደሆነ ገልፀው በተቋሙ በከፍተኛም ሆነ በመካከለኛ ደረጃ ያሉ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ይሄንን አውቀው ማንኛውንም ስራቸውን በግልፅ እና ተጠያቂነት ባለው አካሄድ እንዲሁም ህግና መመሪያን በማክበር መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡ ሙስና የህሊና ጉዳይ ነው፣ ሙስና ሱስ ነው፣ ብልሹ አሠራር አይለኬ ነው ያሉት ዶ/ር ድሪባ ሠራተኞችና ኃላፊዎች ተቋሙና መንግስት ካስቀመጠው ሙስናን የመከላከል፣ የማስወገድ እና የመፀየፍ አቅም በማጎልበት በየተቀመጥንበት ቢሮ በጥንካሬ መስራት እንደሚገባ ሲገልፁ ሴቶች ከታማኝነት እና ሙስናን ከመዋጋት አንፃር ውጤታማ ቢሆኑም ችግሩ ከተፈጠረ ያለምንም ፍርሃት እና መሸማቀቅ በድፍረት እና በጥንካሬ ማጋለጥ እና መዋጋት እንዳለባቸውም አስረድተዋል፡፡ የህግ ማዕቀፎችን ማክበር፣ ደንብና መመሪያዎችን በአግባቡ ማወቅ እና መተግበር የአሰራር ስህተቶችን እና ሆን ብሎ ሙስና ከመፈፀም ይታደጋል በማለት ጨምረው ገልፀዋል፡፡

አቶ ገ/ሕይዎት ወ/ትንሣኤ በኢ.ፊ.ዲ.ሪ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ በሰጡት ስልጠና ከተቋሙ እና ከማዕከላት የበላይ ኃላፊዎች ጋር በቅርበት እና በቅንጅት በመስራት፣ ለሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት የሀብት ምዝገባ ስርዓትን፣ ዕቅድና ሪፖርትን በወቅቱ ማቅረብ፣ የአሠራር ስርዓት ጥናት ማቅረብ ከተጠናም በኋላ መተግበሩን መከታተል እንዲሁም ሞጁል መዘጋጀት እንዳለበት ገልፀዋል፡፡

ወ/ሮ ኤልሣቤጥ ባስልዮስ የተቋሙ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአስቸኳይ ሙስና መከላከል፣ በሃብት ምዝገባ፣ በአሠራር ጥናት እና በሥነ-ምግባርና የሞራል እሴት ግንባታ ላይ ያተኮረ እና በፖወር ፖይንት የታገዘ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የሰጡ ሲሆን በየርዕሱም የቡድን ውይይት ተደርጓል፡፡

ወ/ሮ ተናኜ ኪዳኔ የተቋሙ የሥነ-ምባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ ሪፖርት አፃፃፍን፣ በጥቆማ አቀባበልን እና በቅርቡ የሚከበረውን የዓለም እና የአገር ዓቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን አስመልክቶ ገለፃ አድርገዋል፡፡

በመጨረሻም ዶ/ር ፈቶ ኢስሞ የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የመዝጊያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ የተቋሙ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ተከታታይ የቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች አስቸኳይ ሙስናን ከመከላከል አንፃር ተግተው እንዲሠሩ እንዲሁም ማንኛውንም የተቋሙ እንቅስቃሴ ህግና ደንብ ያከበረ እንዲሆን ከአደራ ጭምር ገልፀው ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

 

Betpasgiris.vip restbetgiris.co betpastakip.com restbet.com betpas.com restbettakip.com nasiloynanir.co alahabibi.com hipodrombet.com nakliyat malatya oto kiralama malatya rent a car eşya depolama istanbul-depo.net eşya depolama sex shop şehirler arası nakliyat evden eve nakliye ofis taşıma şehirler arasi nakliyat ücretleri transfernakliyat.com.tr heceder.org 30 tl deneme bonusu aviator oyunu betexper pdf indir casino siteleri