COVID-19 Response
 

ፍራፍሬ ከምግብነት እስከ ተፈጥሮ ሚዛን ጠባቂነት

አገራችን ኢትዮጵያ  ብዙ አይነት የአትክልትና ፍራፍሬ ብዝሀ ህይወት ካላቸው አገራት መካከል አንዷ ሆና ትጠቀሳለች፡፡ ፍራፍሬ ከስነ-ምግብ አንጻር ሲታይ የንጥረ ነገር ይዘቱ ከፍተኛ በመሆኑ ለሰው ልጅ ምግብነት ተመራጭ ያደርገዋል፡፡ ይሁን እንጂ በአገራችን ካለው የምርት ማነስ የተነሳ የፍራፍሬ አቅርቦት አነስታኛ ነው፡፡ በተለይ  ኢትዮጵያ ካላት የለም አፈር ይዞታ፤ ተስማሚ የአየር ንብረትና ሰፊ የህዝብ ቁጥር አንጻር ካአደጉት አገራት እና ከሌሎች ታዳጊ አገራት ጋር  ሲነጻጸር የፍራፍሬ ምርታችን እና ተጠቃሚነታችን እጅግ አነስተኛ ነው፡፡ 

የፍራፍሬ ምርምር ዘርፍን ለማሳደግ በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የመልካሳ ግብርና ምርምር ማዕከል ላለፉት አምስት አስርት አመታት በፍራፍሬ ምርምር ዘርፍ በርካታ ምርምሮችን ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ በዚህም የተለያዩ የአትክልትና ፍራፍሬ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ፣ በማላመድና በማባዛት ለአርሶ አደሩ በማስተዋወቅ ሰፊ ስራዎችን ሰርቷል፡፡ በአሁን ሰአትም በገጠር ብቻ ሳይሆን በከተሞች አካባቢም ያሉ ነዋሪዎች በጓሮና በደጃፍቸው የፍራፍሬ ችግኝ በመትከል ለምግብ ማዋል እንዲችሉና ከምግብነትም ባሻገር ለገቢያ በማቅረብ ተጨማሪ ገቢ እንያገኙ ግንዛቤን በመፍጠር የምርምር ማዕከሉ ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ጥረትን እያደረገ ይገኛል፡፡ የምርምር ማዕከሉ በአሁን ሰአት በቆላ እና ወይን አደጋ ፍራፍሬዎች ማለትም በፓፓያ፣ ማንጎ፣ አቡካዶና ሙዝ ላይ ሰፊ የምርምር ስራዎችን እያከናወነ ነው፡፡ በዚህም እስካሁን ባለው ሁኔታ ማዕከሉ 3 የፓፓያ፣ 4 የማንጎ፣ 6 የአቡካዶና 14 የሙዝ ዝርያዎችን በምርምር አቅርቧል፡፡

ነገር ግን የፍራፍሬ አምራች አርሶ አደር ቁጥር አሁንም አናሳ መሆኑ ይነገራል፡፡ ሰፊ መሬት እያለን የአርሶ አደሩ የፍራፍሬ ምርቱ ማነስ ምክንያት ምንድን ነው ብለን ላነሳነው ጥያቄ የመልካሳ ግብርና ምረምር ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር በድሩ በሽር ሲመልሱ፤ ፍራፍሬ ከቋሚ ተክሎች ዓይነት እንደሚመደብና ዘርቶና ተክሎ ለምግብነት ለማዋል ረጅም አመታትን ስለሚፈጅ በአርሶ አደሩ ዘንድ ተመራጭ እንዳይሆን አንዱ ማነቆ ሆኗል ብለዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አያይዘውም ይህን ችግር ለመፍታት ከዓመታት በፊት “አንድ ተክል ፍራፍሬ ለአንድ ገበሬ” በሚል እሳቤ ቅስቀሳ ጀምረው ሰርተው እንደነበርም አውስተዋል፡፡ በፍራፍሬ በተለይም በፓፓያ ላይ ረጅም አመታትን በምርምር ላይ ያሳለፍት ዶ/ር ኤዶሳ በበኩላቸው ማዕከሉ መነሻ ቴክኖሎጂ በማቅረብና ለቴክኖሎጂ ተጠቃሚዎች ስልጠናዎችን በመስጠት የሰርቶ ማሳያ ማዕከል በመሆንም  እያገለገለ እንዳለም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ፍራፍሬ ለምግብነት ከመዋሉ በተጨማሪ ለሰው ልጆች ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን ይሰጣል፡፡ ከነዚህም ውስጥ ተረፈ ምርቱ ለእንሰሳት መኖ፣ ለኢንዱስትሪ ግብአትነት፣ የቅርፊትና ቅጠላቸው ብስባሽ ለማዳበሪያነት፣ ለጥላ፣ ለውበትና ለአየር ንብረት ጥበቃ ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ፍራፍሬ ቋሚ ተክል እንደመሆኑ ስነምህዳሩን የመጠበቅና የአየር ንብረት እንዳይዛባ ከመጠበቅ አንጻር ያለው አስተዋጽኦ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ በማዕከሉ የወይን አደጋ ፍራፍሬ ምርምር ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ግርማ ከበደ እንደሚሉት የፍራፍሬ ተክሎች ቋሚና ከራሚ እንደመሆናቸው ውሀን በስራቸው በመያዝ የመሬቱን እርጥበታማነት እንደያዙ የሚቆዩ ሲሆን የአፈር መሸርሸርንም ያስቀራሉ፡፡ ሌላው የዘርፍ ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር አስማረ ዳኜ እንደሚሉት ፍራፍሬ ከምግብነትና ኢኮኖሚን ከመደገፍ ባሻገር ጥምር ደን ሆነው ጥላን በመፍጠርና የአካባቢን ውበት ከመጠበቅ አንጻር ለሰው ልጅ ተስማሚ ናቸው፡፡ በተለይ በአሁን ሰአት በዓለም ላይ ካለው የአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የሆነ ካርቦን ከአየር ላይ ስለሚወስዱና በተመሳሳይ ተክሎቹ የሚተነፍሱትን ኦክስጂን ለሰው ልጆች በመስጠት በዚህም  ከባቢ አየርን በመጠበቅ የተስተካከለ የአየር ንብረት እንዲኖር በማስቻል ጥቅማቸው ዘርፈ ብዙ ነው፡፡ 

ከዚህ አካያ በምርምር የወጡ የፍራፍሬ ቴክኖሎጂዎች አርሶ አደሩ እንዲጠቀምባቸው ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሰፊ ጥረት የሚጠይቅ ሲሆን የምግብ እና የሥነ ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ዘርፉን ውጤታማ ማድረግ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

Betpasgiris.vip restbetgiris.co betpastakip.com restbet.com betpas.com restbettakip.com nasiloynanir.co alahabibi.com hipodrombet.com nakliyat malatya oto kiralama malatya rent a car eşya depolama istanbul-depo.net eşya depolama sex shop şehirler arası nakliyat evden eve nakliye ofis taşıma şehirler arasi nakliyat ücretleri transfernakliyat.com.tr heceder.org 30 tl deneme bonusu aviator oyunu betexper pdf indir casino siteleri