COVID-19 Response
 

ኩታ ገጠም የማምረት ዉጤትና ጎጃም

ግብርና ለአለም ኢኮኖሚ ወሳኝ የሆነ የልማት ዘርፍ ነው፡፡ ያለ ግብርናና የግብርና ውጤቶች የሰውን ልጅ በህይወት የመኖር ህልውና ማሰብ ይከብዳል፡፡ለዚህም የዓለም ሀገራት ህዝባቸውን ለመመገብ የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን ያላቸውን አቅም ሁሉ አሟጠው ለግብርናው አውለዋል፡፡ በዚህም የራሳቸውን ህዝብ ከመመገብ ባለፈ ምርታቸውን ለሌሎች ሀገራት በማቅረብ ኢኮኖሚያቸውን በመደገፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያም ግብርናን ቀድመው ከጀመሩት ሀገራት ተርታ የምትሰለፍ ናት፡፡ይሁን እንጅ ከሌሎች ሀገራት ጋር ሲነጻጸር የሀገራችን ገበሬና ግብርና ይህ ነው ለማለት አያስደፍርም፡፡ ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት ያልተናነሰ የተፈጥሮ ሀብትና ተስማሚ የአየር ንብረት ያላት ሀገር ሆና ሳለ የምርት መጠኗ ግን የሀገር ውስጥ ፍጆታዋንም የሚሸፍን አልሆነም፡፡

ግብርና በአሁን ሰአት በአለም አቀፍ ደረጃ በአንጻራዊነት ሲታይ 80 ፐርሰንት ህዝቧ አርሶ አደር ሆኖ አንድ ገበሬ አራት ቤተሰብ መመገብ የማይችልባት  ሀገር ኢትዮጵያ ናት፡፡ ይህ ለምን ሆነ ብለን ስንጠይቅ ትልቁ ማነቆ ሆኖ የምናገኘው ችግር ሀገራችን የምትከተለው የአስተራረስ፣የአመራረትና የተሻሻሉ ዝርያዎች አጠቃቀም ሂደት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የደብረ ማርቆስ ግብርና ምርምር ማዕከል ይህንን ማነቆ ለመበጠስ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በመስራት ለሌሎች ምሳሌ ለመሆን እየሰራ ይገኛል፡፡ማዕከሉ በአሁን ሰአት ኩታገጠም ቴክኖሎጂ የማስተዋወቅ ስራን በምስራቅና ምእራብ ጎጃም በሚገኙ ዘጠኝ ወረዳዎች ውስጥ የአርሶ አደሮችን መሬት በኩታገጠም በማደራጀት በጤፍ፤በብቅል ገብስ በባቄላ፤በበቆሎና በተለይም በዳቦ ስንዴ በመሸፈን ውጤታማ ስራዎችን ሰርቷል፡፡በምስራቅ ጎጃም ዞን አዋበል፤አነደድ፤ደብረኤልያስ፤ጎዛምንና ባሶ ሊበን ወረዳዎች ላይ ሰፋፊ የኩታ ገጠም የስንዴ ቴክኖሎጂ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ በዘንድው የምርት  ዘመን በሁሉም ሰብሎች በወረዳዎቹ 411.5 ሄክታር መሬትን በ13 ክላስተር በማደራጀት 835 አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ይህ አካባቢ በፊት በነበረው አሰራር አሲዳማ አፈር በመሆኑ ብዙ ምርት የማይገኝበት የእርሻ ቦታ ነበር፡፡በዚህ አመት ግን ደብረ ማርቆስ ግብርና ምርምር ማዕከል አሲዳማ አፈሩን ለማከም የሚያስችል 3040 ኩንታል ኖራ ለአርሶ አደሩ በማሰራጨቱ አመርቂ ውጤት ታይቷል፡፡

ስንዴ በአገራችን ከጤፍ፣ በቆሎና ማሽላ ቀጥሎ በአራተኛ ደረጃ የሚመረት የሰብል አይነት ሲሆን፣ በስንዴ ምርት የሚለማው መሬትም ወደ አንድ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ሄክታር ይጠጋል፡ ፡ ከዚህም የሚገኘው ምርት አምስት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ስንዴ ሲሆን የስንዴ ልማት ምርት መጠኑም በሄክታር 27 ኩንታል ነው፡፡

በባሶ ሊበን ወረዳ የልምጭም ቀበሌ ግብርና ፅህፈት ቤት ሀላፊ ምንያህል ሙሉአዳም አሲዳማ አፈር የአርሶ አደሩ ፈተና እንደነበር ተናግረው በደብረማርቆስ ግብርና ምርምር ማዕከል በተሰራጨ 335 ኩንታል ኖራ መሬቱን አክሞ በስንዴ ሰብል መሸፈን እንደተቻለ ተናግረው 75 ኩንታል የስንዴ ምርጥ ዘር እና 26 ነጥብ 5 ሊትር የፀረ አረም ኬሚካልም ማዕከሉ ድጋፍ በማድረጉ ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን አሳይተዋል። በአጠቃላይ በቀበሌው 2ሺህ 605 ሄክታር መሬት በስንዴ ሰብል የተሸፈነ ሲሆን 1ሺህ 558 አርሶአደሮች በያዘው 26 ክላስተር ላይ 151ሺህ 90 ኩንታል የስንዴ ምርት በዘንድሮው የምርት ዘመን ይጠበቃል።

 በሀገራችን ኢትዮጵያ  አንድ እርምጃ ወደ ፊት በመራመድ ግብርናውን ማዘመን ላይ ትኩረት ቢደረግ ከውጭ የሚገባውን ስንዴ መጠን ከማስቆምም ባለፈ በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ የሆነ የስንዴ ምርት በማምረት የውጭ ምንዛሪን የምናገኝበት ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ይቻላል ያሉት የደብረማርቆስ ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተሩ አቶ ያለው ማዘንጊያ ናቸው፡፡ ይህንን ዓላማ ለማሳካትም ማዕከሉ በአሁን ሰአት የተፈጥሮ ጥበቃን ጨምሮ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚረዱ በርካታ ስራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የኩታ ገጠም እርሻ አላማው የተሻሻሉ ዝርያዎችንና የአሰራር ዘዴዎችን አቀናጅቶ በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ብሎም ቅንጅታዊ አሰራርን ለአርሶ አደሩ በማስተዋዎቅ  ምርታማነትን መጨመር እንደሚቻል ማሳየት ነው፡፡ በዚህም የደብረማርቆስ ግብርና ምርምር ማዕከል አመርቂ ስራዎችን ስርቷል ፡፡በተለይ ኩታገጠም የአስተራረስ ዘዴን ባልተከተሉ አርሶ አደሮች ላይ አወንታዊ ተጽዕኖን በመፍጠር ለላቀ ልማት እንዲነሳሱና ከዘልማዳዊ የአሰራር ዘዴ ወደ ዘመናዊ /መካናይዜሽን /አስተራረስ ለማሸጋገር ያግዛል፡፡የአርሶ አደሩ በኩታ ገጠም የማምረት ፍላጎት መልካም ጅማሮ ይሁን እንጅ ዘመናዊ የእርሻ መሳሪያዎች ማለትም የመዝሪያ፤የማጨጃና የመዉቂያ ግብአቶች አሁንም የአርሶ አደሩ የዘወትር ጥያቄዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም የፌደራሉም ይሁን የክልሉ መንግስት የገበሬውን ችግር ተረድቶ ይህንን ግብአት በማሟላት አርሶ አደሩን ካላስፈላጊ ድካምና የምርት ብክነት ችግር ሊታደገው ይገባል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Betpasgiris.vip restbetgiris.co betpastakip.com restbet.com betpas.com restbettakip.com nasiloynanir.co alahabibi.com hipodrombet.com nakliyat malatya oto kiralama malatya rent a car eşya depolama istanbul-depo.net eşya depolama sex shop şehirler arası nakliyat evden eve nakliye ofis taşıma şehirler arasi nakliyat ücretleri transfernakliyat.com.tr heceder.org 30 tl deneme bonusu aviator oyunu betexper pdf indir casino siteleri