COVID-19 Response
 

ተስፋ የተጣለበት ወርቃማው የሩዝ ማማ በአማራ ክልል

ሩዝ በአለም ላይ  ከግማሽ በላይ ለሚሆነው የዓለማችን ህዝብ ዋና ምግብና የገቢ ምንጭ ነው፡፡ሩዝ ከብዕርና አገዳ ሰብሎች ቤተሰብ የሚመደብ የምግብ እህል ነው፡፡ይህ ሰብል በሀገራችን ኢትዮጵያ በ1970 ዓ.ም አካባቢ መመረት እንደጀመረ የተለያዩ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ሩዝ  በከተሞች አካባቢ በከፍተኛ ደረጃ የሚዘወተር የምግብ አይነት ሲሆን በገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍልም እንዲሁ እየተለመደ መጥቷል፡፡

ኢትዮጵያ ሩዝን ለማምረት የሚያስችል ሰፊ የመሬት አቅም ያላት በመሆኑ በአሁን ሰአት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሩዝን የማምረት ሂደት አበረታች ነው፡፡70 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ የሩዝ ምርት አቅርቦት የሚሸፍነው በአማራ  ክልል መሆኑን መረጃዎች የሚጠቁሙ ሲሆን በያዝነው የምርት ዘመንም በአማራ  ክልል በጣና ተፋሰስ እና አባይ ማዶ በደቡብ ጎንደር ፎገራወረዳ  ላይ በአጠቃላይ 55 ሺህሄክታርመሬትበሩዝሰብልተሸፍኗል::ባህርዳርከተማአስተዳደርዘንዘልማቀበሌ ላይ 519 አርሶአደሮችበኩታገጠምየለማየተሻሻለየሩዝምርትማሳይገኛል፡፡በቀበሌው በኩታ ገጠም  217 ሄክታርመሬትበሩዝምርትየለማሲሆን÷ ከዚህም 10 ሺህኩንታልየሩዝምርትእንደሚገኝ ቅድመ ግምት ተሰጥቶታል፡፡

በደቡብ ጎንደር ፎገራ ወረዳ የሚገኘው የፎገራ ብሄራዊ የሩዝ ምርምርና ሥልጠና ማዕከል የወጣውና ለአርሶአደሩ የቀረበው ሻጋ የተሰኘው የተሻሻለ የሩዝ ዝርያ ድርቅን መቋቋም የሚችልና ምርቱ ከሌሎች ዝርያዎች ቀድሞ የሚደርስ መሆኑ በአርሶ አደሩ ዘንድ ተመራጭ የሆነ ቴክኖሎጂ እንዲሆን አስችሎታል ያሉት የፎገራ ብሄራዊ የሩዝ ምርምርና ሥልጠና ማዕከል ዳይሬክተር ወ/ሮ ሸዋዬ አበራ ናቸው፡፡

በቀደሙት አመታት የጣና ተፋሰስ አካባቢዎች ምንም አይነት ምርት የሚመረትባቸው አካባቢዎች አልነበሩም፡፡የፎገራ ብሄራዊ የሩዝ ምርምርና ሥልጠና ማዕከል የተሸሻሉ የሩዝ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅና በማላመድ በተፋሰሱ ዙሪያ ባሉ 8 ወረዳዎች ላይ “የወደቅ” ሩዝ ማምረት ስራን በማስጀመር የተፋሰሱን  ገጸበረከት እየተጠቀመበት ይገኛል፡፡

በአማራ ክልል ጣና ተፋስስ ዙሪያ ባለው መረጃ መሰረት እሩዝን ማምረት የሚያስችል ወደ 2 ሚሊዮን ሄክታር የሚጠጋ የመሬት ሀብት አለ ያሉት በፎገራ ብሄራዊ የሩዝ ምርምርና ሥልጠና ማዕከል የግብርና ኤክስቴንሽንና ኮሚዩኒኬሽን ምርምር የስራ ሂደት ሀላፊና ተመራማሪ አቶ ምስጋናው አንተነህ ናቸው፡፡ ማዕከሉ በአሁን ሰአት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሩዝ ምርምርን በማስተባበርና የተሸሻሉ የሩዝ ዝርያዎችን በማፍለቅ ወደ ሌሎች ሩዝ የማይመረትባቸው አካባቢዎች የማስፋት ስራ እየተሰራ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

 ‹‹ሻጋ›› በጣናዙሪያበሚገኙ 8 ወረዳዎችላይ 391 ሄክታርመሬትን የሸፈነ ሲሆን  ይህ  የተሻሻለየሩዝዝርያበሄክታር44 እስከ 56 ኩንታልምርትይሰጣልየሚል ተስፋም ተጥሎበታል፡፡ 54 ሴቶችን ጨምሮ 868 አርሶ አደሮች በ47 የኩታ ገጠም አደረጃጀት የተሳተፉበት ሲሆን በተያዘው የምርት ዘመን 17 ሺህ 204 ኩንታል የሩዝ ምርት ይጠበቃል።አርሶአደሩ ካመረተ በኋላ የገበያ ችግር እንዳይገጥመውም ከፎገራ ብሄራዊ የሩዝ ምርምርና ስልጠና ማእከል ጋር በመተባበር  እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አበረታች ናቸው፡፡ ይሁን እንጅ የመዝሪያ ፤የማጨጃና የመውቂያ መሳሪያዎች አሁንም የአርሶ አደሩ ችግሮች ናቸው፡፡

 

 

 

 

Betpasgiris.vip restbetgiris.co betpastakip.com restbet.com betpas.com restbettakip.com nasiloynanir.co alahabibi.com hipodrombet.com nakliyat malatya oto kiralama malatya rent a car eşya depolama istanbul-depo.net eşya depolama sex shop şehirler arası nakliyat evden eve nakliye ofis taşıma şehirler arasi nakliyat ücretleri transfernakliyat.com.tr heceder.org 30 tl deneme bonusu aviator oyunu betexper pdf indir casino siteleri