COVID-19 Response
 

ደብረዘይት ግብርና ምርምር ማዕከል ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አከበረ

በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የደብረዘይት ግብርና ምርምር ማዕከል ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በደማቅ ሁኔታ አክብሮ ዋለ፡፡ የማዕከሉ ሀላፊዎች፤ ተመራማሪዎችና  ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ111ኛ በአገራችን ደግሞ ለ46ተኛ ጊዜ ‘’የዛሬ የፆታ እኩልነት ለነገ ዘላቂነት’’ በሚል መሪ ቃል በትላንትናው ዕለት በማዕከሉ የስብሰባ አዳራሽ የማዕከሉ ሰራተኞች የተለያዩ ዝግጅቶችን በማቅረብ አክብረው ውለዋል፡፡

ዶ/ር ዳኘ ሞጆ የማዕከሉ ዳይሬክተር በመክፈቻ ንግግራቸው ቀኑ የሴቶች ይባል እንጂ የወንዶችም ጭምር ሲሆን ቀኑን ስናከብር ሴቶች በማህበራዊ እና በኢኮኖሚው ዘርፍ የሚያበረክቱትን ሁለንተናዊ አስተዋጽዎ በመዘከር መሆን እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ በዓለም ላይ ሴቶች ከወንዶች ባልተናነሰ መልኩ ያበረከቱትን ሥራ አጉልተን የምንዘክርበትም እና ወደፊትም ሴቶች ያለባቸውን የቤተሰብ ጫና በማቃለል በግብርና ምርምር ሚናቸውን ለማጎልበት ማገዝ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

በማዕከሉ የግብርና ኤክስቴንሽን አስተባባሪ የሆኑት ወ/ሮ ጥሩዓይነት መኩሪያው በበኩላቸው ይህንን ቀን ስናከብር በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በማለፍ ለታላቅ ደረጃ የበቁ ሴቶችን በመዘከር እና ትውልዱን በመቅረጽ የበኩላችንን ድርሻ መወጣት እንዳለብን በማሰብ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በኢንስቲትዩቱ የሥርዓተ ፆታ ምርምር አስተባባሪ የሆኑት ወይዘሮ ለምለም አበበ ደግሞ ይህን የሴቶች ቀን ስናከብር በዓለም አቀፍ ደረጃ ሴቶች ለመብታቸው የከፈሉትን ትልቅ ዋጋ ማሰብ እንደሚገባ እና በቀጣይም የሴቶችን እኩልነት ለማረጋገጥ ብዙ መስራት እንዳለብን ማስታወስ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሴቶችን መብትና እኩልነት ለማረጋገጥ አንድ ክፍለ ዘመን እንደሚወስድ የገለጹ ሲሆን እንደ ምርምር ተቋም ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ቴክኖሎጅዎችን ማፍለቅ፤ በዘመናዊ የእርሻ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክህሎታቸውን ማጎልበት እና በአመራር ቦታ በእኩልነት ማሳተፍ በግብርናው ዘርፍ ብሎም ለሀገር እድገት ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡

በዝግጅቱ ላይ በማዕከሉ ተመራማሪ ወይዘሮ ውብሸት ጭጨ የቀረበውን ጽሁፍ መሰረት በማድረግ የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱም ላይ ስኬታማ የሆኑ የማዕከሉ ሰራተኞች የህይወት ልምድና ተሞክሯቸውን አካፍለዋል፡፡ በመጨረሻም የሴቶችን ጥቃት የማይቀበል ትውልድ ለመፍጠር ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል በሚል መልዕክት ዝግጅቱ ተጠናቋል ፡፡

Betpasgiris.vip restbetgiris.co betpastakip.com restbet.com betpas.com restbettakip.com nasiloynanir.co alahabibi.com hipodrombet.com nakliyat malatya oto kiralama malatya rent a car eşya depolama istanbul-depo.net eşya depolama sex shop şehirler arası nakliyat evden eve nakliye ofis taşıma şehirler arasi nakliyat ücretleri transfernakliyat.com.tr heceder.org 30 tl deneme bonusu aviator oyunu betexper pdf indir casino siteleri