As a national research institute, EIAR aspires to see improved livelihood of all Ethiopians engaged in agriculture, agro-pastoralism, and pastoralism through market-competitive agricultural technologies.

Latest News

EIAR IN THE MEDIA

የጭሮ ብሔራዊ የማሽላ ምርምርና ስልጠና ማዕከል ለምዕራብ ሐረርጌ ዞን አርሶ አደሮች የተሻሻለ የማሽላ ቴክኖሎጂ አስተዋወቀ

የጭሮ ብሔራዊ የማሽላ ምርምርና ስልጠና ማዕከል ሥራ ከጀመረበት 2006 ዓ.ም. ጀምሮ በዋናነት በማሽላ ምርምር ላይ በማተኮር እየሰራ የሚገኝ ማዕከል ሲሆን በሂደትም የማሽላ ምርምር ልቀት ማዕከል በመሆን ተፈላጊ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅና በማላመድ የአርሶ አደሩን ሕይወት ለመለወጥ በሰፊው እየሰራ ይገኛል፡፡

ማሽላ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጠቃሚ ሰብል ሲሆን ለምግብነት፣ ለእንስሳት መኖነት እና ለአልኮሊክ መጠጦች መስሪያነት በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ በኢትዮጵያ ለእርሻ ከሚውለው መሬት ውስጥ ከጤፍና በቆሎ ቀጥሎ በሶስተኛ ደረጃ በማሽላ ሰብል የሚሸፈን ሲሆን አጠቃላይ ከሰብል ከሚገኘው ምርት ማሽላ ከበቆሎ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ እስካሁን ድረስ በተደረገው አገራዊ የምርምር ስራ በአጠቃላይ ከ60 በላይ የሚሆኑ የማሽላ የተሻሻሉ ዝርያዎች ለተለያዩ  የማሽላ አብቃይ አካባቢዎች ለምርት ተለቀዋል፡፡ ከእነዚህ ተሻሽለው ከተለቀቁ የማሽላ ዝርያዎች መካከል በቅርቡ በመልካሳ ግብርና ምርምር ማዕከል የተገኘው ‹‹መልካም›› የተሰኘውን ዝርያ ከጭሮ ብሔራዊ የማሽላ ምርምርና ስልጠና ማዕከል ጋር በመተባበር ምዕ/ሐረርጌ አንጫራ ወረዳ ለሚገኙ አርሶ አደሮች አስተዋውቆአል፡፡ 

የምርምር ማዕከሉ ሚያዝያ 22 ቀን 2009 ዓ.ም. በምዕራብ ሐረርጌ አንጫር ወረዳ አነኖ ቀ/ገ/ማ/ ከአርሶ አደሮች ጋር በጋራ ያከናወናቸውን የቴክኖሎጂ ማስተዋወቅ ስራዎች አስመልክቶ የመስክ ቀን ጉብኝት ያካሄደ ሲሆን በጉብኝቱ ላይ ማዕከሉ ከመልካሳ ግብርና ምርምር ማዕከል የተገኘውን የማሽላ ዝርያ ማስተዋወቅና ማስፋፋት ላይ የሰራው ስራ ተጎብኝቷል፡ የማዕከሉ ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ዘውዱ በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩቱ ይህ ‹‹መልካም›› የተባለው ዝርያ የዝናብ እጥረት እና ድርቅን ተቋቁሞ በ3 ወር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ምርት የሚሰጥ መሆኑንና በተለይ በምስራቅ ሐረርጌ እስከ ምዕራብ ሐረርጌ ለሚኖሩ አርሶ አደሮቸ በምግብ ዋስትና ራሳቸውን ለማስቻል ትልቅ ሚና ሊጫወት የሚችል ዝርያ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በመስክ ቀኑ ጉብኝት በዓሉ ላይ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፈንታሁን መንግስቱ፣ የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ መስፈን አሰፋ፣ የዞንና ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ሃላፊዎች፣ የማዕከሉ ተመራማሪዎች፣ አርሶ አደሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፈንታሁን መንግስቱ በመስክ ጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት የሰብል ምርት ምርታማነትን ለማሳደግ በአገር ደረጃ በሁሉም አካባቢ በሰፊው ለመስራት ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን ልማቱን የሚገዳደሩ እንደ አየር ንብረት ለውጥ ያሉ ክስተቶች እየተከሰቱ ያሉበት ሁኔታ ቢኖርም ከዚህ አንፃር ማሽላ ይህንን አስቸጋሪ የአየር ፀባይ ለውጥ እንደ ዝናብ አጠር አካባቢዎችንና ድርቅን ተቋቁሞ የምግብ ዋስትናን ሊያረጋግጥ የሚችል ትልቅ ተስፋ የሚጣልበት ሰብል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አክለውም ኢንስቲትዩቱ ከሚሰራባቸው ሰብሎች መካከል ማሽላ በተለይም የብዕርና አገዳ ተብለው ከሚጠሩት አምስት ሰብሎች አንዱና ዋነኛው መሆኑን ገልፀው በምርምሩ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተገኙ የማሽላ ዝርያዎች መካከል እንደ መልካምና ደቀባ የተሰኙ ዝርያዎች በአጭር ጊዜ የሚደርሱ እዚህ አካባቢ የተሞከሩ ልዩ ባህሪ ያላቸውና የዝናብ እጥረትንና ድርቅን ተቋቁመው በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ በሄክታር ከ45-50 ኩንታል ምርት ሊሰጡ የሚችሉ ዝርያዎችን ለሁሉም በተለይ ዝናብ አጠር ለሆኑ አካባቢዎች ለማዳረስና የአርሶ አደሩን ምርታማነት በማሻሻል የምግብ ዋስትና ችግር መፍታትና ገቢውን ለማሳደግ በሰፊው እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡  

ምርምር ማዕከሉ ባደረገላቸው የዘር አቅርቦትና ሙያዊ ድጋፍ የማሽላ ምርትና ምርታማነታቸው እንደሚያድግ በመስክ ቀን  ምልከታ ላይ የተሳተፉ አርሶ አደሮች ገልፀዋል፡፡ አርሶ አደር ሱልጣን መንገሻ ይባላሉ በምዕ/ሐረርጌ ዞን አንጫራ ወረዳ ነዋሪ ናቸው ከአሁን በፊት በተለመደው የአመራረት ዘዴ ድርቅን መቋቋም የማይችል ከ6-9 ወራት የሚፈጅ በሄክታር ከ5-10 ኩንታል የማይበልጥ የማሽላ ምርት እንደሚያገኙ ገልፀው በአሁን ወቅት ከምርምር ማዕከሉ ጋር በመተባበር  አሻሻሎ  በሰጣቸው ‹‹መልካም›› የተሰኘ ምርጥ የማሽላ ቴክኖሎጂ ማስተዋወቅ እና በተደረገላቸው ሙያዊ ድጋፍ ከሄክታር ከ45-50 ኩንታል ሊያገኙ እንደሚችሉ ገልፀዋል፡፡ ሌላኛዋ አርሶ አደር ሰዒዶ ከድር ይባላሉ እሳቸውም እንደገለፁት ምርምር ማዕከሉ ባደረገላቸው ድጋፍ በክላስተር በመደራጀት ቴክኖሎጂውን ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀው ከሄክታር ከ45-50  ኩንታል እንደሚያገኙ ተናግረዋል፡፡ 

በሌላ በኩል በዚሁ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ አርሶ አደሮች ከላይ የተጠቀሰውን ድርቅን መቋቋም እና ለዝናብ አጠር አካባቢዎች ተስማሚ የሆነውን የማሽላ ዝርያ ለመጠቀም ያልሞከሩ በመሆኑ ለቀጣይ የአካባቢዉ አርሶ አደሮች በሙሉ ተሳታፊ የሚሆኑበት መንገድ ቢመቻች እና አስፈላጊው የዘር አቅርቦት እንዲሁም ዘመናዊ የመስኖ አጠቃቀም ልምድ መሟላት እንዲኖርበት ጉዳዩ ለሚመለከታቸው መስክ ቀኑ ተሳታፊዎች ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

 

Upcoming Events

 • External Project Review Meeting

  Organizer: Planning Monitoring and Evaluation Directorate

  Venue: EIAR HQ, Training Room

  From:  April 25-27, 2018

 • Awareness Creation Training for new researchers

  Organizer: Agricultural Economics Research Directorate

  Venue: EIAR HQ, Training Room

  From:  April 23-24, 2018

 • Mid-Term Project Progress Review Meeting

  Organizer: BMGF-MERCI Project

  Venue: EIAR HQ, Training Room

  From:  April 20-21, 2018

 • Regular Planned Meetings and Trainings

  Organizer: BMGF-MERCI Project

  Venue: EIAR HQ, Training Room

  From:  April 09-18, 2018

Research Areas

Research Centers