As a national research institute, EIAR aspires to see improved livelihood of all Ethiopians engaged in agriculture, agro-pastoralism, and pastoralism through market-competitive agricultural technologies.

Latest News

EIAR IN THE MEDIA

 

 

የፎገራ ብሔራዊ የሩዝ ምርምርና ሥልጠና ማዕከል ለደቡብ ጎንደር ዞን አርሶ አደሮች የተሻሻለ የሩዝ ቴክኖሎጂ አስተዋወቀ

የፎገራ ብሔራዊ የሩዝ ምርምርና ሥልጠና ማዕከል ጥቅምት 26 ቀን 2010 ዓ.ም. በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ ያከናወናቸውን የምርምር ሥራዎች ከአርሶ አደሮችና ሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት መስክ ቀን ጉብኝት አካሄደ፡፡

የፎገራ ብሔራዊ የሩዝ ምርምርና ሥልጠና ማዕከል ከተቋቋመበት 2005 ዓ.ም. ጀምሮ በዋናነት በሩዝ ምርምር ላይ በማተኮር እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎንም የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት እና በተለያዩ በሀገሪቷ አካባቢዎች የሚከናወነውን ብሔራዊ የሩዝ ምርምር ፕሮግራም የማስተባበር ስራም ይሰራል፡፡

የማዕከሉ ዳይሬክተር ዶ/ር ጥላሁን ታደሰ በመስክ ጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ዕድሜ ያለው ቢሆንም ቀደም ሲል በአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል በሩዝ ሰብል ላይ ሲሰራ የነበረውን ምርምር በመረከብ በርካታ ሥራዎችን በማከናወን ላይ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሰው በአካባቢው ለሚገኙ አርሶ አደሮች በክረምት ወራት የሚለሙ የሩዝ ሰብል በተጓዳኝ በመስኖ የሚለሙ ዓመታዊ የአትክልት እና ቋሚ የፍራፍሬ ሰብሎች ላይም የምርምር ስራን እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አክለውም ማዕከሉ ከተባባሪ ማዕከላት ጋር በጋራ በመስራት ከተመሰረተ ባስቆጠረው ጥቂት ዓመታት ውሰጥ ስድስት የሩዝ ዝርያዎችን ያስለቀቀ መሆኑን እና የተለያዩ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የአቅም ግንባታ ስልጠና ለባለሙያዎች እና ለአርሶ አደሮች የሰጠ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ 

ምርምር ማዕከሉ ባደረገላቸው የዘር አቅርቦትና ሙያዊ ድጋፍ የሩዝ ምርትና ምርታማነታቸው እንደሚያድግ በመስክ ቀን ምልከታ ላይ የተሳተፉ አርሶ አደሮች ገልፀዋል፡፡ አርሶ አደር ገደፋው መኳንንት ይባላሉ በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ ቁሃር ሚካኤል ነዋሪ ናቸው እሳቸው እንደሚሉት ሩዝን ከአሁን በፊት በተለመደው የአመራረት ዘዴ የሚያመርቱ ቢሆንም ውጤቱ ግን አጥጋቢ እንዳልነበር ገልፀው በአሁን ወቅት ከምርምር ማዕከሉ ጋር በመተባበር ዝርያውን አሻሻሎ በሰጣቸው ‹‹ኤክስ ጀግና›› የተሰኘ የሩዝ ቴክኖሎጂ እና በተደረገላቸው ሙያዊ ድጋፍ ከሄክታር ከ20-25 ኩንታል ሊያገኙ እንደሚችሉ ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም ምርምር ማዕከሉ ባደረገላቸው ድጋፍ በማህበር በመደራጀት የሩዝ ቴክኖሎጂ የብዜት ስራ በመስራት ተጠቃሚ መሆናቸውን በዚሁ ቀበሌ በማህበር የተደራጁ ዘር አባዥ አርሶ አደሮች ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል በዚሁ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ አርሶ አደሮች ይህን ‹‹ኤክስ ጀግና›› የተሰኘ የተሻሻለ የሩዝ ቴክኖሎጂ ያልተጠቀሙ መሆናቸውን ገልፀው፤ በመሆኑም ለቀጣይ የአካባቢዉ አርሶ አደሮች በሙሉ ተሳታፊ የሚሆኑበት መንገድ ቢመቻች እና አስፈላጊው የዘር አቅርቦት እንዲሟላላቸው ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የመስክ ቀኑ ተሳታፊዎች ጠቁመዋል፡፡

በመጨረሻም ማዕከሉ ያከናወናቸውን ሰርቶ ማሳያ ማሳዎችን ጨምሮ በአካባቢው በማህበር የተደራጁ ዘር አባዥ አርሶ አደር  ማሣዎች ጉብኝት ተካሄዶል፡፡ በመስክ ቀን በዓሉ ላይም የኢንስቲትዩቱ የሥራ ኃላፊዎች፣ የዞኑና የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የማዕከሉ ተመራማሪዎች፣ አርሶ አደሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል፡፡

 

 

Upcoming Events

Research Areas

Research Centers