News

ኢንስቲትዩቱ በከተማ ግብርና ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሄደ

የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በግማሽ ምዕት ዓመት ጉዞው ለግብርናው ምርት እድገት ግብዓትነት የሚውሉ በርካታ የግብርና እውቀት፣ ቴክኖሎጂና መረጃዎችን በማቅረብ ዛሬ ለተደረሰበት አገራዊ የግብርና ልማትና ኢኮኖሚያዊ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡ በዚሁ ረገድ ምርታማነት እና ጥራትን የሚጨምሩ የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶ አደሩ፣ አርብቶ አደሩ እና ከፊል አርብቶ አደሩ በማፍለቅ፣ በማላመድ፣ በማስተዋወቅ እና ፍላጎትን በመፍጠር እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡

ተቋሙ የአገሪቱን ሥነ-ምህዳር በመከተል በስሩ የሚገኙ የፌደራል የምርምር ማዕከላትን በማስተባበር እና ከሌሎች  መንግስታዊ ካልሆኑ የልማት ድርጅቶች እና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ይሰራል፡፡ በዚሁ መሠረት (Center for Development and Capacity Building –CDCB) ከተባለ በልማትና አቅም ግንባታ ዙሪያ ከሚሰራ ተቋም ጋር በመተባበር በከተማ ግብርና ዙሪያ ግንቦት 25 ቀን 2010 ዓ.ም. በዋናው መ/ቤት ህሩይ አዳራሽ ምክክር አካሄዶአል፡፡

የምክክር መድረኩ ዓላማ በአዲስ አበባ አካባቢ ኦሮሚያ ፊንፊኔ ልዩ ዞን ያሉ አርሶ አደሮች በከተማ ግብርና ያሉ ዕድሎችን እና የተገኙ ልምዶችን ከዚሁ ከልማት ድርጅት ጋር በመተባበር በተቀናጀ ሁኔታ መስራት የሚቻልባቸውን መንገዶች መሠረት በማድረግ የሴክተሩን ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ ምክክር ለመካሄድ የታቀደ ነው፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ማንደፍሮ ንጉሴ የምክክር መድረኩን በከፈቱበት ወቅት እንደተናገሩት የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ እንዲህ አይነት ምክክር መካሄዱ እንደ መልካም ተሞክሮ የሚወሰድ መሆኑን ጠቅሰው  የከተማግብርናየከተማነዋሪዎችንኢኮኖሚያዊናማህበራዊአቅምከማሳደግምባለፈየአየርንብረትለውጥንለመቋቋምየሚያበረክተውአስተዋጽኦየጎላነው፡፡ ስለሆነም ኢንስቲትዩቱ የከተማ ግብርና ፖሊሲ ቀርፆ ተግባራዊ እንዲሆን በጥናት የተደገፈ ሰነድ ለመንግስት ለማቅረብ እንቅስቃሴ መጀመሩንም ገልፀዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ኢንስቲትዩቱ የምርምር ተቋም እንደመሆኑ መጠን የተለያዩ ምርትና ምርታማነትን የሚጨምሩ ቴክኖሎጂዎችና መረጃዎች የሚፈልቁ በመሆኑ በከተማ ዙሪያ የሚኖሩ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንደዚህ ካለ የልማት ድርጅቶች ጋር በጋራ መስራት ወሳኝ በመሆኑ የምክክሩን መድረክ አስፈላጊነት አብራርተዋል፡፡

በምክክር መድረኩ ላይ የሌሎች አገሮች በከተማ ግብርና ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች እና የተገኙ ውጤቶችን የዳሰሰ ፅሑፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ የማዕከል ዳይሬክተሮች፣ የፊንፊኔ ልዩ ዞን ግብርና ኃላፊዎች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ነበሩ፡፡

 

Events