የአሜሪካ ተምች ምንድን ነው?

አሜሪካን ተምች (Fall armyworm [Spodoptera frugiperda]) መነሻው በመካከለኛው አሜሪካ ሲሆን በሌፒዶፕቴራ ምድብ በኖክቲዩዴ  ቤተሰብ ውስጥ የሚመደብ የእሳት ራት ትል ነው፡፡ ወደ አህጉራችን አፍሪካ እንዴት እንደገባ እስከ አሁን ድረስ ግልፅ ባይሆንም፤ለመጀመሪያ ጊዜ //አ ጃንዋሪ 2016  ናይጄሪያ ውስጥ ሪፖርት መደረጉ ታውቋል፡፡ በመቀጠልም ወደ መካለኛው አፍሪካ በመስፋፋት //አ በኤፕሪል 2016 ክስተቱ ሪፖርት ተደረገ፡፡ በመቀጠልም በዲሴምበር 2016 በደቡብ የአፍሪካ ሀገራት በወረርሽኝ ደረጃ ተከሰተ፡፡

በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ //አ በፌብሪዋሪ 2017 በየኪ ወረዲ ሸካ ዞን ውስጥ በመስኖ በተዘራ የበቆሎ ማሳ ውስጥ መከሰቱ ሪፖርት ተደረገ፡፡ በአሁኑ ወቅትአገራችንን ጨምሮየአፍሪካ ሀገራት በተባዩ እየተጎዱ ሲሆን በተለይም በቆሎን በተመሳሳይ ወቅት በሚያለሙ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ስጋቱ ከፍተኛ እየሆነ መቷል፡፡

በተባዩ የሚጠቁ ሰብሎች

አሜሪካ ተምች 100 የሚበልጡ የተለያዩ የሰብል ዓይነቶችን የሚያጠቃ ቢሆንም በተመራጭነት እንደ በቆሎ፣ስንዴ፣ገብስ፣ማሽላ፣ዳጉሳ፣የሸንኮራ አገዳ፣አኩሪ አተር፣ድንች፣ጥጥ እንዲሁምአትክልቶችንና የተለያዩ ቅጠለ-ሰፋፊ ሰብሎችንና አረሞችን አብዝቶ የሚመገብ ሲሆን ሌሎች የሣር ዝርያዎችንም (Gramineae) እንደሚመገብ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

የተባዩ መለያ ዘዴዎች

ትሉ ጭንቅላቱ ላይ በሚታየው ነጭ የተገለበጠ Y” ቅርጽ የሚለይ ሲሆን በተለይም ከተለመደው ተምች በጀርባውይ በሚገኙት እሾክ ባላቸው ጥቁር ጉብጉብ ያለ ቅርጾችና በሻካራው ሰውነቱ ይለያል፡፡ የወንዴው የእሳት ራት የፊት ክንፍ ግራጫና ቡናማ ሲሆን የላይኛው ጠርዝና የክንፉ መሀል ላይ የማዕዘን ቅርፅ ያላቸው ነጭ ነጠብጣቦች ይታያል፡፡ የሴቷሳት ራት የፊት ክንፍ ግን በግልፅ የሚታይ ምልክት ባይኖረውም ነጣ ባለ ግራጫማ ቡና ዓይነት መደብ ላይ የተዥጎርጎሩ ግራጫና ቡናማ ምልክቶች ይታያሉ፡፡

 

ዕንቁላል

ዕንቁላሎቹ ከስር ጠፍጣፋና ከላይ ሾጣጣ ሲሆኑ ነጣ ያለ እና ወደ (Pink) የሚጠጋ ቀለም አላቸው፡፡ በአንድ ጊዜ የሚጣለው ዕንቁላል ብዛት ከቦታ ቦታ ቢለያይም 100 እስከ 200 ዕንቁላል ይደርሳል፡፡አንድ ሴት የእሳት ራት በአማካይ 1500 ዕንቁላሎችን የምትጥል ሲሆን ከፍተኛው 2000 እና ከዚያ በላይ ሊሆን ይችላል፡፡ዕንቁላሎቹ አንዳንድ ጊዜ ተደራርበው የሚጣሉ ሲሆን በአብዛኛው በነጠላ በቅጠሎች ላይ ተጣብቀው ይጣሉና ሴቷ የእሳት ራት ፀጉር ወይም ሻጋታ በሚመስል ሽፋን ትሸፍናቸዋለች፡፡ንቁላሎቹ በአብዛኛው ከቅጠሎች የስረኛው አካል ላይ የሚጣሉ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ከላይኛው አካል ላይም ይጣላሉ፡፡ዕንቁላሎቹ ለመፈልፈል 2-3 ቀናትይፈጅባቸዋል፡፡

 

ትል

ትሉ 6 የዕድገት ደረጃዎች ሲኖሩት እንደተፈለፈለ በጣምአነስተኛና 1.7 /ሜ የሚደርስ አረንጓዴ ሲሆን ጭንቅላቱ ጥቁር ነው፡፡ 2ኛውና በ3ኛውየዕድገት ደረጃ ላይ ጭንቅላቱ ብርቱካናማ ቀለም ሲኖረው 4ኛው እስከ 6ኛው የዕድገት ደረጃው ጀርባው ወደ ቡናማነት ይለወጣል፡፡ በጀርባው ላይ እሾክ ያለው ጥቁር ጉብጉብ ያለ ቅርፅ እና በጭንቅላቱ ላይ ነጭ የተገለበጠ “Y” ቅርጽ ይታይበታል፡፡ ቀን ላይ ትሎቹ ራሳቸውን የመደበቅ ባህሪ አላቸው፡፡በቡድን የሚከሰተው ትል ዕድገቱን ለመጨረስ እንደ አየሩ የሙቀት ሁኔታ 14 እስከ 30 ቀናት የሚወስድበት ሲሆን በእህልና የግጦሽ ሳር ላይ ከፍተኛ ጉዳትያደርሳል፡፡

 

ኩብኩባ

ዕድገቱን የጨረሰው ትል 2-8 /ሜ ጥልቀት አፈር ውስጥ ሰር ስሮ በመግባት ሽፋን የሌለው 20-30 /ሜ የሚረዝም የዕንቁላል ቅርጽ ወዳለው ኩብኩባ ይለወጣል፡፡አፈሩ ግን ጠንካራ ከሆነበት ከወዳደቀ ቅጠልና በአካባቢው ከሚገኘው ማቴሪያል ከአፈር በላይ ቀፎ በመስራት ወደ ኩብኩባነትይለወጣል፡፡ኩብኩባው ቀይ ቡናማ ቀለም ሲኖረው ርዝመቱ በአማካይ 14-18 /ሜ የሚደርስ ሲሆን 4.5 /ሜ ስፋትአለው፡፡በአመቺ የአየር ሁኔታ ወቅት የኩብኩባው ቆይታ 8-9 ቀናት የሚወስድ ሲሆን በቀዝቃዛ ወቅትግን 20-30 ቀናት ብሎም ቅዝቃዜው ካየለ እስከ 55 ቀ ት ሊፈጅ ይችላል፡፡ ቅዝቃዜው ለረጅም ጊዜ ከቆየ መቋቋም አይችልም፡፡

 

የእሳት ራት

የእሳት ራቶች በመጀመሪያው የምሽት ሠዓት ላይ ከኩብኩባው ይወጣሉ፡፡ ክንፋቸው ሲዘረጋ 32-40 /ሜ ይረዝማል፡፡የሁለቱም ጾታዎች የኋላ ክንፍ የሚያንጸባርቅ ብርማ ነጭ ሲሆን ቀጠን ያለ ጥቁር ጠርዝ አለው፡፡ የእሳት ራቶቹ የሚንቀሳቀሱት ማታማታ ሲሆን ሞቃታማና ዕርጥብ በሆኑ ምሽቶች የበለጠ ይንቀሳቀሳሉ:: ሴቷ የእሳት ራት ወንዱን ፍለጋ እስከ 480 ኪ/ሜ የመብረር አቅም ያላት ሲሆን ወንዱን ለመሳብምሴክስ ሆርሞን ታመነጫለች፡፡ ሴቷ የእሳት ራት ከተፈለፈለች 3-4 ቀናት በኋላ በመጀመሪያዎቹ 4-5 ቀናት አብዛኛውን ዕንቁላል የምትጥል ሲሆን የተወሰኑትን ደግሞ እስከ    3ኛው ሳምንት ድረስትጥል ትችላለች፡፡ የእሳት ራቶቹ አማካይ የዕድሜ ቆይታ 10 ቀኖች ሲሆን እንደየ ሁኔታው 7-21 ቀናትመኖር ይችላሉ፡፡

 

አሜሪካ ተምች ጉዳት

ትሉ እንደተፈለፈለ ቅጠሉን በአንድ በኩል ብቻ በመፋቅ ይመገብና 2ኛና 3ኛ የዕድገት ደረጃ ላይ ሲደርስ ቅጠሎቹን በመብሳት ከጠርዝ ጀምሮ ይመገባል፡፡በተክሉ ሙሽራ ውስጥም በመግባት ስለሚመገብ ቅጠሎቹ ሲያድጉ በመስመር የተደረደሩ ቀዳዳዎች ይታያሉ (እንደ በቆሎ አገዳ ቆርቁር)፡፡ በተጨማሪም በደረሰ የበቆሎ ፍሬና በመውጣት ላይ ባለ አበባ ላይ ይመገባል፡፡ይህ ተባይ በጣም ጠንካራ መንጋጋ ስላለው በተክሉ በማንኛውም የዕድገት ደረጃ በሁለም የተክሉ ክፍል ላይ በመመገብ በምርት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል፡፡ 

  

በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ ተምች ስርጭት በኢትዮጵያ

በደቡብ ክልል

·         በ12 ዞኖች

·         በ72 ወረዳዎች

·         በ1009 ቀበሌዎችና

·         በ17 ሺህ 737 ሄክታር የበቆሎ ማሳ ላይ ተከስቷል፡፡

 

በኦሮሚያክልል

·         በ5 ዞኖች

·         በ27 ወረዳዎች

·         በ251 ቀበሌዎችና

·         በ5 ሺህ 163 ሄክታር የበቆሎ ማሳ ላይ ተከስቷል፡፡

 

የመከላከያና መቆጣጠሪያ ዘዴዎች

የእሳት ራቶቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ ረጅም ርቀት በመጓዝ የሚዛመቱ በመሆናቸው፣በከፍተኛ ቁጥር የመራባት አቅም ስላላቸው፣ የተክሉን የዕድገት ክፍል (ሙሽራውን) ስለሚያጠቁ፣ ትሉ በመጀመሪያው የዕድገት ደረጃውይ በተክሉ ሙሸራ ውስጥ ገብቶ ስለሚመገብና ፀረ- ተባይ ስለማያገኘው አንዳንዴ ፀረ-ተባዮችን በቀላሉ የመቋቋም ባሕርይ እያሳየ መሆኑ ተባዩን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ውጤታማ አያደርገውም፡፡በመሆኑም ይህን ተባይ ለመከላከል በመቀጠል የተዘረዘሩትን እና ውጤታማነታቸው በምርምር የተረጋገጠውን የመከላከያ ዘዴዎች ሁሉ አቀናጅቶ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ ክትትልና ቅድመ ትንበያ የዚህ ተባይ ክትትልና ቅድመትንበያሥርዓትእንደአፍሪካተምች (Spodoptera exempta) ቀላል ባይሆንም አርሶ አደሩና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በሙሉ አስፈላጊውን ወቅታዊ ክትትል በማድረግ ለሚመለከተው ክፍል ሪፖርት ማድረግ፣ለዚህ ተባይ ተብሎ የተዘጋጀ ፌርሞን ወጥመድ በመጠቀም ከጎረቤት ሀገሮች የክስተትመረጃ ጋር በማቀናጀት የቅድመ ትንበያ ሥርዓቱን በአፋጣኝ መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡

 

የመከላከያ መንገዶች

የበቆሎ ማሳን ከአረሞች በተለይም ለተባዩ መሸሸጊያ ሊሆኑ የሚችሉ የሳር ዝርያዎችን ማጽዳት /ማስወገድ፣ማሳውን በጥልቀት በማረስ/በመገልበጥ ኩብኩባውና ትሉ ለፀሃይ እንዲጋለጥ ማድረግ፤ሁልጊዜ አዝመራው ከተሰበሰበ በኃላ ማሳው ላይ የቀሩ ቅሪቶችን በማቃጠል ማስወገድ::

 

የመቆጣጠሪያ መንገዶች

1. ባህላዊመቆጣጠሪያ ዘዴዎች፡-በቆሎን በተባዩ ከማይጠቁ ሰብልችጋር መማሰባጠርና በማፈራረቅ መዝራት፤ቀደምብሎ መዝራት፤ ሲደርስምቀደም ብሎ መሰብሰብ፡፡

 

2. ፀረ-ተባይ መጠቀም

·         ትሉ እንደተፈለፈለ በሙሽራው ውስጥ ስለሚገባና በንክኪ በሚገድሉ ፀረ-ተባዮች ተባዩን መቆጣጠር አስቸጋሪ ስለሆነ ከርጭት በፊት ትሉ ያለበትን የዕድገት ደረጃ በጥንቃቄ መለየት ያስፈልጋል፡፡

·         በቆሎ ከተዘራ በኋላ በመጀመሪያዎቹ 30 ቀናት ውስጥ በቡቃያ ላይ 5% የመቆረጥ ወይም 20% ጥቃት በሙሽራው ላይ ከታየ፣ እንዲሁም በማሽላ ሙሽራ ውስጥ 1-2 ወይም በማሽላው ራስ ላይ 2 ትል ከታየ

o   ማላታይን፣

o   ክሎርፓይሪፎስ፣

o   ፐርመትሪን፣

o   ላምዳሳያሎትሪንእናለተምችመከላከል ጥቅምላይየሚውሉትንፀረ-ተባዮችመጠቀምይቻላል፡፡

 

የመረጃ ምንጭ፡-በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የበቆሎ ምርምርና የሰብል ጥበቃ ምርምር ቡድን