በኢንስቲትዩቱ በስርዓተ-ፆታ ምርምር ዙሪያ ሥልጠና ተሰጠ

በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በቴክኖሎጂ ስርፀትና ኮሜርሻላይዜሽን ምርምር ዳይሬክቶሬት አማካይነት ከሁሉም ማዕከላት ለተውጣጡ የስርዓተ-ፆታ ምርምር ተወካዮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ከሚያዝያ 24 – 26/2010 .. በዋናው /ቤት ተሰጥቷል፡፡ 

የስልጠናው ዓላማ በዋናነት ስርዓተ- ፆታ ምርምር ከግብርናው ዘርፍ ጋር ያለውን ትስስር እንዲሁም የስርዓተ-ፆታ መተግበሪያ መሣሪያዎችን (gender analysis tools) በመጠቀም በግብርና ምርምሩ ሥርዓት ውስጥ በስርዓተ-ፆታ ምርምር ዙሪያ የሚሰሩ ስራዎች ግምገማ ሂደት ላይ የተወካዮቹን ዕውቀትና ክህሎት ለማሳደግ መሆኑን የገለፁት ስልጠናውን የሰጡትና በዋናው /ቤት የሥርዓተ-ፆታ ተጠሪ የሆኑት / ለምለም አበበ ናቸው፡፡ 

/ ለምለም እንደገለፁት በኢንስቲትዩቱ ሥርዓተ- ፆታን በምርምር ሥርዓት ውስጥ አካቶ በመስራት በኩል መልካም ጅምሮች እንዳሉ በመግለፅ ይህንኑ ጅምሮ በሁሉም የምርምር ሂደት ውስጥ ለማስረፅ በማዕከላት ያሉትን የሥርዓተ- ፆታ ምርምር ተወካዮችን አቅም መገንባት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡