COVID-19 Response
 

በደቡብ ወሎ የመጀመሪያውን የፌደራል የግብርና ምርምር ማዕከል ለመገንባት የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ፡፡

የግብርና ሚኒስትር ክቡር አቶ ዑመር ሁሴን፣ በአማር ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ ክብርት ወ/ሮ አይናዓለም ንጉሴ፣ የአማር ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶ/ር ኃ/ማርያም ከፍያለ፣ የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የአ/የአቅም ግንባት ም/ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር ችሎት ይርጋ፣ የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳዳሪ ክቡር ዶ/ር አብዱ ሁሴን እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት አንዲሁም የአካባቢው አርሶ አደሮች በተገኙበት በደቡብ ወሎ ዞን በወረኢሉ ወረዳ የመጀመሪያውን የፌደራል የግብርና ምርምር ማዕከል ለማስገንባት ግንቦት 9 ቀን 2014 ዓ.ም የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ፡፡

በመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ ሥርዓት ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የወረኢሊ ወረደ አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን አይቼው የግብርናውን ምርታማነት ለማሳደግ እና ተወዳዳሪ ለማድረግ አርሶ አደርች የግብርና ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እና ለገበያ የሚያመርቱ መሆን እንዳለባቸው በመግለጽ በምርምር የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎች፣ ለእንስሳት እና ለተፈጥሮ ሀብት ልማት የሚያገለግሎ የግብርና ቴክኖሎጂዎች ለአካባቢው አርሶ አደሮች በስፋትና በተከታታይ ለማቅረብ በወረኢሉ ወረዳ የግብርና ምርምር ማዕከል ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ በመጣሉ በወረዳው ህብረተሰብ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳዳሪ ዶ/ር አብዶ ሁሴን በመክፈቻ ንግግራቸው በዞኑ የግብርና ምርምር ማዕከል ለማቋቋም ለቀረበውን ጥያቄ በሚኒስቴር መ/ቤቱ ይሁንታ አግኝቶ ለዚህ ቀን በመብቃታችን በዞን መስተዳደርና ህዝብ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የዞኑ አስተዳደር ከፍተኛ የሆነውን የአርሶ አደሩን የቴክኖሎጂ ፍላጎት ለሟሟላት ከኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ጋር በቁርጠኝነት አንደሚሰሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ 

በሥነ ሥርዓቱ ላይ ለተደረገው ደማቅ አቀባበል የግብርና ሚኒስትር ክቡር አቶ ዑመር ሀሴን ምስጋና በማቅረብ በወረዳው የግብርና ምርምር ሊገነባ በመሆኑ ለአካባቢው ማህበረሰብ እና አርሶ አደሮች እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል፡፡ ክቡር አቶ ዑመር ሁሴን አያይዘውም የሀገራችን ኢኮኖሚ የተመሰረተው በግብርና ላይ በመሆኑ የግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ በምርምር ካልተደገፈ የምንፈልገውን እድገት ማስመዝገብ እንደማይችል እና በማደግ ላይ የሚገኘውን የሀገራችን ህዝብ መመገብ እንደሚያዳግት ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም በዞኑ የሚስተዋሉትን የምርታማነት ማነቆዎች በምርምር እና በቴክኖሎጂ ለመፍታት እና የህዝቡን ጥየቄ መሰረት በማድርግ በወረዳው የግብርና ምርምር ማዕከል ለማቋቋም ዝግጅቶች መጀመራቸውን ገልጸው የአካባቢው አርሶ አደሮች የምርምር ማዕከሉን የህብረተሰቡ ሀብት መሆኑን በመረዳት አስፈላጊውን ትብብር እና አጋርነት እንዲያደርጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ 

በአማር ክልል በም/ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ ክብርት ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ በበኩላቸው የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ ውጤታማ ልናደርግ የምንችለው የግብርና ቴክኖሎጂዎች አቅርቦት በማሻሻልና እና ተደራሽነት በማድረግ ሲሆን ለገበያ እና ለኢንደስትሪ ግብዓት የሚሆን ትርፍ ምርት በማምረት የአርሶ አደሩን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ተግቶ መሥራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የአማር ክልል የግብርና ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ኃ/ማርያም ከፍያለ በንግግራቸው በታሪክ እንደምንረዳው የወረኢሊ ወረዳ ቀደምት አባቶቻችን የውጪ ጠላትን ድል ለማድረግ ምክር የመከሩባት፣ ስልት የቀየሱባት ከተማ ስትሆን አባቶቻችን በሰሩት አኩሪ ታሪክ አሁን ያለው ትውልድ ለዚህ ቀን መብቃት መቻሉን አብራርተዋል፡፡ ስለሆኑም የአሁኑ ትውልድ ድህነትን ለማጥፋት ታሪክ መስራት እንደሚገው ዶ/ር ኃ/ማርያም ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ችሎት ይርጋ ኢንስቲትዩቱን በመወከል የአንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የአርሶ አደሩን የቴክኖሎጂ ፍላጎት ለሟሟላት ከማዕከል ግንባት ጎን ለጎን ከቀጣይ የምርት ዘመን ጀምሮ ወደ ሥራ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም የአካባቢው ህብረተሰብ ተወካዮች ገለጻ ያደረጉ ሲሆን በወረዳው የግብርና ምርምር ማዕከል ለመገንባት የመሰረተ ድንጋይ መቀመጡ ለወረዳው ብሎም ለዞኑ አርሶ አደሮች የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ፋይዳ ያለው ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎን ሌሎች መሰረት ልማቶች መሟላት እነደሚገባ ተናግረዋል፡፡

 

 

 

Betpasgiris.vip restbetgiris.co betpastakip.com restbet.com betpas.com restbettakip.com nasiloynanir.co alahabibi.com hipodrombet.com nakliyat malatya oto kiralama malatya rent a car eşya depolama istanbul-depo.net eşya depolama sex shop şehirler arası nakliyat evden eve nakliye ofis taşıma şehirler arasi nakliyat ücretleri transfernakliyat.com.tr heceder.org 30 tl deneme bonusu aviator oyunu betexper pdf indir casino siteleri