የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የተሻሻለው የተመራማሪዎች የዝውውር መመሪያ ቁጥር …. /2016

  • Post author:
  • Post category:Resources
  • Post comments:0 Comments
  • Reading time:1 mins read

በኢንስቲትዩቱ በየጊዜው በሚፈጠሩ ክፍት የሥራ መደቦች ላይ ተመራማሪዎችን በዝውውር ለማሰራት ወይም በጤና ወይም በቤተሰብ
ችግር ወይም ተቀባይነት ባላቸው በሌሎች ምክንያቶች ከሠራተኛው የዝውውር ጥያቄ ሲቀርብ፣ ጥያቄው ግልጽና ወጥነት ባለው
ሁኔታ ህጋዊ የአሰራር ስርዓትን ተከትሎ ተግባራዊ ማድረግ በማስፈለጉ ነባሩን መመሪያ አሻሽሎ በሥራ ላይ ማዋል አስፈልጓል፡፡
ከዚህ አኳያ በፌደራል መንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 የወጣውን የፌደራል የመንግስት ሠራተኞች የዝውውር
መመሪያ መሠረት በማድረግ የኢንስቲትዩቱን የአሠራር ሥርዓት እንዲሁም የምርምሩን የሥራ ባህሪ ከግምት ውስጥ በማስገባት
በኢንስቲትዩቱ ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 527/2015 አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ 21 መሰረት ይህ የተሻሻለው የተመራማሪዎች የዝውውር
መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡

Leave a Reply