የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የዘር፣ ሌሎች የምርምር ውጤቶችእና የተረፈ ምርት ሽያጭ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር …/ 2016

  • Post author:
  • Post category:Resources
  • Post comments:0 Comments
  • Reading time:1 mins read

ኢንስቲትዩቱ የባለድርሻ አካላት ፍለጎት ለማርካት ጥራትና ወቅቱን የጠበቀ እንዲሁም
በዘመናዊ የቴክኖሎጂ ብዜት ስርዓት አምርቶ ለተጠቃሚዎች ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም
ኢንስቲትዩቱ የተቀላጠፈ የሽያጭ ሥርዓት በመጠቀም ተልዕኮውን ለመወጣት እንዲያስችለው
በየማዕከሉ ከምርምር የሚገኙ የምርምር ምርቶችና ተረፈ ምርቶች ሲሸጡ በቂ ቁጥጥርና
የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት አስፈልጓል፤
ስለሆነም ለኢንስቲትዩቱ የዘር፣ ሌሎች የምርምር ውጤቶችና ተረፈ ምርት ሽያጭ ሂደት
የሚመራበት አሰራር ተግባራዊ ማድረግ እንዲቻል፤ በሽያጭ ሥራዎች ውስጥ ሊተገበሩ
የሚገባቸውን ዝርዝር መስፈርቶችን በማካተት በሽያጭ ሥራ ላይ የሚሳተፉ አካላት
እንዲገለገሉበት፤ ወጥነት ያለው የባለድርሻ አካላት ዕርካታና ገፅታ መገንባት አስፈልጓል፤
በዚህ መነሻ የመንግሥት ህጎች፣ የሌሎች መሰል ተቋማትን የአፈፃፀም ልምድ በማገናዘብ፣
የባለድርሻዎችን ፍላጐት ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት እንዲሁም በንስቲትዩቱ ማቋቋሚያ ደንብ
527/2015 አንቀጽ 6(4) የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት ኃላፊነትና ተጠያቂነትን በየደረጃው
በማስቀመጥ ይህ የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የዘር፣ ሌሎች የምርምር
ውጤቶች እና የተረፈ ምርት ሽያጭ አፈፃፀም መመሪያ ነባሩን መመሪያ ቁጥር …… በማሻሻል
ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡

Leave a Reply