****************************************
የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት
ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም.
በኢንስቲትዩቱ ለአራት ዓመታት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ክቡር ዶ/ር ፈቶ ኢስሞ የሽኝት ፕሮግራም ተደረገላቸው፡፡ የሽኝት ፕሮግራሙ ዶ/ር አበራ ደሬሳ የተቋሙ የቦርድ ሰብሳቢ፤ ዶ/ር ብርሃኔ ገ/ኪዳን የተቋሙ የቦርድ አባል፤ የማዕከላት አመራሮች፤ ሠራተኞችና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት ተከናውኗል፡፡ በአንፃሩም አዲስ ለተሾሙት ፐሮፌሰር ንጉሴ ደቻሳ የአቀባበል መርሐ-ግብር ተከናውኗል፡፡
በሽኝት እና በአቀባበል መርሐ-ግብሩ ላይ የኢንስቲትዩቱ የም/ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ድሪባ ገለቲ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ሽኝት ለሚደረግላቸው ለክቡር ዶ/ር ፈቶ ኢስሞ የመልካም ዕድል ምኞት አዲስ ለተሾሙት ፐሮፌሰር ንጉሴ ደቻሳ ደግሞ መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው በራሣቸውና በተቋሙ ሠራተኞች ስም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡
በመርሐ-ግብሩ የተቋሙ የዋና መስሪያ ቤትና የማዕከላት ሰራተኞችና አመራሮች ለክቡር ዶ/ር ፈቶ ኢስሞ የስጦታ ማስታወሻ አበርክተውላቸዋል፡፡

