You are currently viewing የዋሸራ በግ ዝርያን በማሻሻል

የዋሸራ በግ ዝርያን በማሻሻል

  • Post author:
  • Post category:News
  • Post comments:0 Comments
  • Reading time:2 mins read

የዋሸራ በግ ዝርያን በማሻሻል የአርቢውን ማኅበረሰብ ዘላቂ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየተሠራ ነው

የዋሸራበግ ዝርያን በማሻሻል የአርቢውን ማኅበረሰብ ዘላቂ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየተሠራ መሆኑን በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የደብረ ማርቆስ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ፡፡

የዋሸራ በግ ዝርያ ለማሻሻል ከማሕበረሰብ ጋር በመተባበር የተሠራ ሥራ ላይ ያተኮረ የመስክ ጉብኝት ተካሂዷል።

በወቅቱ የማዕከሉ ዳይሬክተር አቶ ያለው ማዘንጊያ እንደተናገሩት፤ የማኅበረሰቡን ፍላጎት መሰረት ያደረገ እና አሳታፊ የበግ ዝርያን በማሻሻል አርቢውን ማኅበረሰብ ዘላቂ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየተሠራ ነው፡፡

ከበግ ዝርያዎች መካከል አንዱ የሆነው የዋሸራ ዳንግላ በግ ዝርያ በዋናነት በኢትዮጵያ ካሉ የበግ ዝርያዎች ጋር ሲነፃፀር ተወዳዳሪ እንዲሁም የተሻለ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመው፤ በምዕራብ ጎጃም ፣ ምስራቅ ጎጃም እና አዊ ዞኖች እንዲሁም በመተከል ዞንና በደቡባዊ የጣና ሐይቅ አካባቢዎች በስፋት ተሰራጭቶ የሚገኝ የበግ ዝርያ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በኢትዮጵያ 14 የሚደርሱ የበግ ዝርያዎች መኖራቸውን እንዲሁም የዋሸራ በግ ዝርያ ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ የሥጋ ገበያ ከፍተኛ ድርሻ የሚኖረው የበግ ዝርያ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

የዋሸራ በግ ዝርያ በአማካይ በውልደት ጊዜ 2 ነጥብ 8 ፣ በጡት መንጠፍ ጊዜ 13 ነጥብ 8 እና በስድስት ወር 17 ነጥብ 87 ኪሎ ግራም በአንድ ዓመት 23 ነጥብ 47 ኪሎ አካባቢ እንደሚመዝኑ ገልፀዋል፡፡

ሴቶቹ በአንድ ዓመት ውስጥ ለመውለድ ብቁ ሆነው የጠራ ዘር የሚገኝበት ሁኔታም መማቻቸት መቻሉን ገልፀዋል፡፡

ሰኔ 22 ቀን 2015 ዓ.ም

Leave a Reply