የፌዴራል መንግሥት መ/ቤቶችና ተቋማት እንደተቋማቸው የሥራ ባህሪያት የራሳቸውን
የሥራ ልብስ፤ የሥራ መሣሪያና ቁሳቁሶችን አጠቃቀም መመሪያ አዘጋጅተው መጠቀም
እንዲችሉ በነሐሴ 14 ቀን 2000 ዓ.ም በቁጥር መ.30/ጠ57/20/334 ከቀድሞው የፌዴራል
ሲቪል ሰርቪስ ኤጀንሲ በተጻፈ ደብዳቤ በተሰጠው መመሪያ መሠረት የኢትዮጵያ የግብርና
ምርምር ኢንስቲትዩት በኢንስቲትዩቱ ዋና መስሪያ ቤትና በስሩ ላሉት የምርምር ማዕከላት
እንደ ማዕከላቱ የሥራ ባህርይና ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ የሚያገለግል የሥራ ልብስና የሥራ
መሥሪያዎች አሰጣጥና አጠቃቀም መመሪያ አውጥቷል፡፡