ኢንስቲትዩቱ የሠራተኞችን ዕውቀትና ክህሎት በተሻለ ሁኔታ ለመጠቀም ከሚገለገልባቸው
ስልቶች መካከል ለምርምር ሥራ ምቹ የሥራ አካባቢን ከመፍጠር ጋር ተያይዞ ሠራተኞች
ምርምሩ በሚካሄድበት አካባቢ በቅርበት በመኖር የምርምሩን ሥራ በተረጋጋ ሁኔታ
እንዲያከናውኑ የመኖሪያ ቤት በተገነባላቸው ማዕከላት የመኖሪያ ቤት አገልግሎት ማቅረብ
አስፈላጊ ነው፡፡
በመሆኑም በነባሩ መመሪያ ላይ የነበሩ ክፍተቶችን ለማሻሻል፣ በአዲሱ የኢንስቲትዩቱ
አደረጃጀት ምክንያት የተፈጠሩ የሥራ መደቦችን ለማካተት እና ከወቅቱ ጋር የሚጣጣም
የተሻሻለው የኢንስቲትዩቱ የመኖሪያ ቤትና የመገልገያ ዕቃዎች ድልድልና አጠቃቀም መመሪያ
ወጥቷል፡፡