መመሪያ ቁጥር…/2018

  • Post author:
  • Post category:Resources
  • Post comments:0 Comments
  • Reading time:1 min read

የግብርና ምርምር እና አገልግሎት ተቋማት ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አሰጣጥና ቁጥጥር መመሪያ

በሀገራችን የሚከናወኑ የግብርና ምርምር እና አገልግሎቶች የግብርና ልማቱን ፍላጎት ለማሟላት ተወዳዳሪና ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል፤ የቁጥጥር ሥርዓት በመዘርጋት አጋዥ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን የማፍለቅ፣ የማበልጸግና የማላመድ ሂደት ቀጣይነትን ማረጋገጥ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

የግል ዘርፉ የየአካባቢዎችን ልዩ የልማት ጸጋዎችን መሠረት ያደረገ የቴክኖሎጂ ማፍለቅና ማላመድ ተግባር ላይ ተወዳዳሪ ሆኖ የሚሰራበት ግልጽ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤

በግብርና ምርምር ወይም አገልግሎት ላይ መሰማራት ለሚፈልጉ ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የሚሰጥበት መስፈርቶችና ቁጥጥር የሚደረግበትን የአሠራር ሂደቶች የሚዘረጋ የህግ ማዕቀፍ ባለመኖሩ፤ ይህንኑ በግልፅ መደንገግ በማስፈለጉ፤

የግብርና ሚኒስቴር የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 አንቀጽ 19 ንዑስ አንቀጽ 4 እና አንቀጽ 20 ንዑስ አንቀጽ 1 (ሸ) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡

Leave a Reply