መመሪያ ቁጥር …. / 2017

  • Post author:
  • Post category:Resources
  • Post comments:0 Comments
  • Reading time:1 min read

የግብርና ምርምር ሥርዓት አጋርነት መወሰኛ መመሪያ

በሀገራችን የሚከናወኑ የግብርና ምርምር ወይም አገልግሎት የግብርና ልማትን ፍላጎት ለማሟላት ተወዳዳሪና ውጤታማ እንዲሆን ለማስቻል፤

የብዝሀ ተዋንያን አጋርነት ሥርዓት በመዘርጋት የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ፣ በማበልጸግ፣ በማላመድ፣ መረጃዎችን በማውጣት፣ አእምሯዊ ኃብቶችን በመጠበቅ እና የሚሰጡ አገልግሎቶችን ተደራሽነት በማስፋት የልማቱን ቀጣይነት ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ፤

የግብርና ምርምር ትግበራን ወይም አገልግሎት መስጠትን በጋራ በማከናወን በዘርፉ ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት የሚፈልቁና የሚላመዱ ቴክኖሎጂዎች እና አገልግሎቶች የግብርና ሥነ-ምህዳርን ያማከሉ፣ የተጠቃሚ ፍላጎትን የሚያሟሉ፣ ችግር ፈቺና በገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማድረግ፤

በግብርና ምርምር ወይም አገልግሎት አጋርነት ለመሰማራት ለሚፈልጉ የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ የምርምር ተቋማት ግልፅነትን፣ ተጠያቂነትን እና በመተማመን አብሮ መስራትን ለማረጋገጥ የሚያስቸል የሕግ ማዕቀፍ በማስፈለጉ፤

በግብርና ምርምር ወይም አገልግሎት አጋርነትን ለመፍጠር፣ በአጋርነቱ ውስጥ የሚኖሩትን መብትና ግዴታዎች ለማስተዳደርና ለማስፈጸም፣ አጋርነትን ተከትለው የሚመጡ ፕሮጀክቶችን በጋራ ለማስተዳደር እና የአጋር አካላትን ጥቅም በአግባቡ ለማስጠበቅ የሚያስችል ወጥ የሆነ የህግ ማዕቀፍ ቀርጾ መተግበር የግብርና እና ገጠር ልማት ፖሊሲው በዚህ ረገድ ያስቀመጠውን አቅጣጫ እውን ለማድረግ ወሳኝ በመሆኑ፤      

የግብርና ሚኒስቴር በአስፈጻሚ አካላት ስልጣንና ተግባር መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 1263/2014 አንቀጽ 20 ንኡስ አንቀፅ 1 (የ) እና አንቀፅ 19 ንዑስ አንቀፅ (4) በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡

Leave a Reply